|
|
| ሊኒክስ
ምንድነው?
|
ሊኒክስ
የነጻ ኦፕሬቲንግ
ሲስተም ሲሆን ላኑስ
ቶርቫልድስ በሚባል
ግልሰብ እንደ
አውሮፓውያን
አቆጣጠር 1991 አ/ም ተማሪ
በነበረበት ጊዜ
ተፈጠረ። በመጀመሪያ
ያቀረበው የሊኒክስን
ከርናል (ወይም
አስኳል) ሲሆን -
ይህንንም የሊኒክስ
ሶፍትዌር በነጻ/ክፍት
ሶፍትዌር ፋውንዴሽን
አማካኝነት
ለተጠቃሚው ህዝብ
ቀረበ።
ከጊዜ
ወደጊዜ የዚህን ነጻ
ሶፍትዌር አመሰራረት
በመደገፍ በርካታ
የሶፍትዌር ጥሬ-ደንብ
እድገት ተሳታፊዎች
(ወይም ሶርስ ኮድ
ዲቬሎፐርስ) ለእድገቱ
አስተዋጽኦ
አበርክተዋል፣
እያበረከቱም ነው።
የሊኒክስ ሶፍትዌር
ጥሬ-ደንብ (ሶርስ ኮድ)
በነጻ ለማንም
ግልጋሎት ውሏል፣
ማንም በዚሁ እድገት
መሳተፍ፣ ማሻሻል እና
ማበልጸግ ይችላል።
አሰራሩም በሊኒክስ
ኮሚዩኒቲ መዋቅር
የተገነባ ስለሆነ፣
የሶፍትዌር አዋቂዎች
የሰሩትን ማሻሻያና
እርማቶች
ለኮሚዩኒቲው
በማቀረብ እድገቱ
በተቀላጠፈ መንገድ
እንዲቀጥል
አስችሏል።
የሊኒክስ እድገት ነጻ
የሃሳብና ሶፍትዌር
ልውውጥ ባህል ላይ
የተመረኮዘ ሲሆን፣
በሶፍትዌር ጥሬ-ደንብ
እድገት ተሳታፊዎች
(ዲቬሎፐርስ) መካከል
ክፍት የግንኙነት
መድረክ መፍጠርም
አይነተኛ ተግባሩ
ነበር። ተቀዳሚው
የግንኙነት መድረክም
ኢንተርኔት ሲሆን
ለሶፍትዌሮች ነጻ
ልውውጥም ይህ መድረክ
ተቀዳሚ መገልገያ
ሆነ።
ሊኒክስ በአሰራር
ተመሳሳይ ሆኖ
የቀረበውና
በዴስክቶፕ ጸባይ
እንዲቀመጥ ታስቦ
የተሰራው አንጋፋው
ኦፕሬቲንግ ሲስተምስ -
ዩኒክስን በዴስክቶፕ
ለማስቀመጥ ታስቦ
የተሰራ ሲስተም ነው።
በጊዜያችን፣ በርካታ
ዩኒክስ አይነቶች
እንዳሉ (AIX, HPUX, Sun Solaris...)
እንደዚሁም የነጻው
ኦፕሬቲንግ ሲስተምስ -
ሊኒክስም በርካታ
አይነቶች አሉት (Redhat, Suse, Ubuntu,
Melderik, Slackware...)ጥቂቶቹ ናቸው።
ምንም እንኳን ከርናሉ
የኦፕሬቲንግ
ሲስተሙን ጸባይ
ቢመሰርትም፣
ለመስራት
የምንፈልገውን
ተግባር ለማከናወን
በሚጠቅመን መልክ
ማሻሻል የተፈቀደ ነው
ብሎም የተለመደ
አሰራር ነው። ሁሉም
የሊኒክስ አይነቶች
የሚጠቀሙት አንድ
አይነት ከርናል ሲሆን
ይህም ሁኔታ ሁሉም
የሊኒክስ አይነቶች
በሚከተሉት ጸባዮች
ላይ ተመሳሳይነት
እንዲኖራቸው
ያደርጋል።
- በርካታ
የሰራ ክንውኖችን
(ወይም
መልታይታስኪንግ)
ማካሄድ
- በርካታ
ተጠቃሚዎች
ማገልገልን፣ ወይም
መልታይዩዘርስ
- በተጠቃሚውና
በዴስክቶፑ መካከል
ግራፊካል መገናኛ
መልክን ማቅረብ
- ቁሳቁሶችን
(ሀርድዌር) መደገፍ
- ኔትወርክ
ግንኙነቶችንና
ሰርቨሮች ለሚሰጡት
ግልጋሎት ድጋፍን
መስጠት
- የተለያዩ
ሶፍትዌሮች ክንውን
እንዲኖራቸው
ማድረግን መሰረታዊ
ናቸው።
ወደጥያቄው
ለመመለስ ሊኒክስ
ታዲያ ምንድነው?የታወቀ
ዴስክቶፕና ሰርቨር
ኦፕሬቲንግ ሲስተም
ሲሆን፣ በተለይ
በሰርቨር አካባቢ
ምናልባት ከ70% በአለም
ላይ ያሉ ሰርቨሮች
በዚሁ ኦፕሬቲንግ
ሲስተምስ የተገነቡ
ሲሆን፣ ምናልባት
በሙሉ የኢንተርኔት
ሰርቪስ ሰጪዎች በዚህ
ኦፕሬቲንግ ሲትም
የተመሰረቱ ናቸው።
በመጀመሪያ አመጣጡ
ዩኒክስን በዴስክቶፕ
ላይ ለማስቀመጥ
ሲሆን፣ ከዚሁም ጋር
የዩኒክስ ዋጋ
ውድነትና የላይሰንስ
ክፍያ ትንሽ
ካንፓኒዎችን ብቻ
ሳይሆን ለትልልቅ
ካንፓኒዎችም ጫና
ነበር። የሊኒክስ
መከሰት ከጊዜ በኋላ
ይህንን ችግር ማቃለል
ብቻ ሳይሆን፣
የሶፍትዌር ወጪንና
ላይሰንስ ክፍያን
አስመልክቶ
አጠፋቸው። በአሁኑ
ጊዜ ካንፓኒዎች
የሊኒክስን ነጻ
ሶፍትዌር በመጠቀም
ወጪያቸው
ለአድምንስትሬተሮች፣
ለአይ.ቲና፣
ማይክሮሶፍት
ሲስተምስ የሚያወጡት
ወጪ ብቻ ነው
ያለባቸው።
|
|
እዚህ
ላይ አንዱ ችግር፣
የሊኒክስ ሲስተሞች
እንድ እንዳንጋፋው
ዩኒክስ በትክክል
ሴታፕ ለማድረግ ጊዜ
ይጠይቃል።
ከማይክሮሶፍት
ዊንዶውስ ሲስተሞች
ጋር ሲወዳደር ሁሉ
ነገር ግራፊካል
ለማድረግ ቢሞከርም
ደንዳና ሲስተም
ለመፍጠር
ኮማንድላየን መጠቀም
የምንገደድበት ጊዜ
ትንሽ አይሆንም።
ነገር ግን አንዴ ሴታፕ
ከሆነ በኋላ ባልታወቀ
ምክንያት
እንደዊንዶውስ
ሲስተም ውድቀቶችና
የሴኪዩሪቲ ችግሮች
የሉበትም ማለት
ይቻላል።
የግንባታችን
መሰረት
ቀጥሎም
ለሰርቨር ግንባታ
መሰረት የሆኑና
ትኩረት
የማደርግባቸው የስራ
መመሪያ (ሮድ ማፕ)
የሚከተሉትን
በመመለስ
የተስተካከለ
ክላይንት/ሰርቨር
ግንባታ ማድረግ
ይቻላል።
-
የሚያስፈልጉ
የሰርቨር ቁሳቁሶች
(Hardware) ፕላን ማድረግ
- ሰርቨር ለመገንባት
የተነሳንበትን የስራ
ጸባይ መመርመርና
ለዚሁ ተግባር ክንውን
የሚጠቅሙ ሰርቪሶች
ላይ በቂ ጥናት ማድረግ
- ለኦፕሬቲንግ
ሲስተሙና ለስራችን
የመረጥናቸው
ሰርቪሶች (servers)
ተግባራዊ ክንውን
የሚጠይቁትን የሜሞሪ
መጠን ማስላት
- ተመሳሳይ ታስኮችን
(ሬደንደንሲ) ማስወገድ
(ይህ ህግ ሳይሆን፣
ለኛ ተግባር
የመረጥነው የስራ
ጸባይ ነው)
- ስታንደረድ
ላይ የተመሰረተ
ኔትወርክ መገንባት
- የኔትወርክ
አወቃቀራችን፣
ሰርቨሩን ጨምሮ፣
ባለው ላይ ወደፊት
ለማደግ የሚችል
(ስኬለብል) እንጂ
የነበረውን ሁሉ
አስወግደን አዲስ
እንድንገነባ
የሚጠይቀን መሆን
የለበትም
- በፐብሊክና ሎካል
ኔትወርክ መካክል
ፋየርወል መገንባት
- የኔትወርካችንን
ጤንነት ለመጠበቅ
የኔትወርክ
ማናጅመንት ሶፍትዌር
መጠቀም
- ማንም ተጠቃሚ
ኔትወርክ ለመገልገል
ማንነቱን ማሳወቅ
ይኖርበታል
- ሊኒክስን
በምንገነባበት ጊዜ፣
የኦፕሬቲንግ
ሲስተሙን መሰረት
ካስቀመጥን በኋላ
አንድ ባንድ ከላይ
በቁጥር 2 ያቀድናቸውን
ሰርቨሮች መገንባት፣
ወይም ኦፕሬቲንግ
ሲስተሙን
በምንገነባበት ጊዜ
ሰርቨሮችንም አብሮ
መገንባት ሁለት
አማራጮች ሲሆኑ፣
በዚህ ጽሁፍ
የምጠቀምበት
የሁለተኛውን ይሆናል
- ኦፕሬቲንግ
ሲስተሙንና
ሰርቨሮችን ከገነባን
በኋላ የሚከተለው
ተግባር ማስላት (configuration)
ይሆናል፣ ተቀባይነት
ባለው አሰራር ዘይቤ
ላይ ማተኮር
- በመጨረሻም
ስራችንን መመርመር፣
ይህም የዴስክቶፕ
ኮምፒዩተሮቻችንን
ማገናኘት ይሆናሉ።
ልበወለዳዊ
ንግድ የስራችን መነሻ
ስራችን
ጣእም እንዲኖረው
ልበወለዳዊ በሆነ
ካንፓኒ የንግድ ስሙ
ተስፋ ኢንኮርፖሬሽን (tesfa
inc) የሚባል መሰረት
በማድረግ የሰርቨር
ግንባታችንን
ከኔትወርክ ጋር
በማጣመር የሚኖረውን
ሂደትና ክንውን
በመልኩ ማቅረብ
የበለጠ አቀራረቡን
ያጣፍጠዋል ብዬ
በመገመት፣ ካሁን
በኋላ የሚኖረውን
ሂደት በዚሁ
ልበወለዳዊ ካንፓኒ
ላይ መሰረት በማድረግ
ከንግዱ እድገት ጋር
የኔትወርኩን
አገልግሎት ጎን ለጎን
አብሮ በማስኬድ
የተፈለገውን
ግልጋሎት ለመስጠት
እንዴት እንደሚረዳና
ትልቅ የወጪ መፍትሄ
እንደሆነም ለማሳየት
እሞክራልሁ።
|
|
|
|
እዚህ
ላይ ወጪን መቀነስ
የሚለውን አሰራር
አውትሶርሲንግ
ከሚለው ጋር አናማታው
ምክንያቱም እንደኛ
አይነቱ አገር በዚህ
መርህ ተጠቃሚ ይሆናል
ብዬ አልገምትምና
የሱም ሃሳብ አቀንቃኝ
አይደለሁም።
ምክንያቱም በቀሩት
አለማት በቂ መልስ
ያልተሰጠበትና
እድገቱ አለማዊ
የካፒታል መስፋፋት
ጋር የተያያዘ ሲሆን፣
በአገሮች ባህል፣
ታሪክ፣ ምጣኔ ሀብትና
የስነ-መንግስት
መዋቅር ላይ የሚኖረው
ጣልቃ ገብነት በሰፊው
እየታየም ስለሆነ
ነው። የበለጠ ውይይት
በዚህ ላይ
አልከፍትም።
አውትሶርሲንግንና
የካፒታል አለም
አቀፋዊ የበላይነት
አላማ በሚመለከት
በርካታ የተጻፉ
መጽሐፍቶች ስለሚኖሩ
እነሱን
እንድትመለከቱ
አስተያየቴን
በመስጠት
ወደአላማችን
እመለሳለሁ።
አቶ
አደፍርስ በአዲስ
አበባ ኗሪ ሲሆኑ
አብዛኛውን
የኢትዮጵያን ክልሎች
ያውቃሉ። ይህም
የሆነው በተለያዩ
ላኪና አስመጪ መስሪያ
ቤቶች ስለሰሩ
የሚላኩትን እቃዎች
መጠን ለማወቅ ወይም
የተጠየቁትን እቃዎች
ለመደራደር ብሎም
አዲስ ክላይንቶችን
ለማግኘት በሚሰሩበት
መ/ቤት ስም ሆነው
በመቶ ሺዎችና
በሚሊዮን ብሮች
የሚቆጠሩ ድርድሮችን
አካሂደው የሰሩበትን
መ/ቤት ሀብታም
አድረገዋል።
አሁን
አቶ አደፍርስ የግል
ንግድ ለማቋቋም
ከፍተኛ ጥረት ላይ
ሲሆኑ፣ ስሙ ተስፋ
ኢንኮርፖሬሽን
ይባላል ከላይ
እንደተጠቀሰው።
ይህም ንግድ የተለያዩ
ራፍሬዎችን በየቦታው
ለሚገኙ ሆስፒታሎችና
ፍራፍሬ አቅራቢ
ግሮሰሪዎች ማከፋፈል
ሲሆን፣ በርካታ
ጨረታዎችን አሸንፈው
በተቀላጠፈ መንገድ
ንግዳቸውን ለመጀመር
ከፍተኛ ጥድፊያ ላይ
ናቸው። ቢሮዋቸውንም
ቦሌ መንገድ ከሚገኝ
አንድ ውብ ህንጻ ውስጥ
ተከራይተዋል።
ለዚህ
ስራ ክንውን
ካለጥርጥር
የሚያስፈልጋቸው
አንድ በኮንትራት
የሚሰራና በሚፈልጉት
ጊዜ ብቻ የሚገኝ
ኮምፒዩተሮችን
ለቢዝነሳቸው
በሚያመች መልክ
የሚያስተካክል
(ኮንሳልታንት) ፣
አንድ አካውንታንት፣
አንድ ማርኬቲንግ
የሚሰራ ወደፊት
ቢዝነሳቸውን
ለማስፋት በርካታ
ፕላኖች ስላላቸው
ለዚሁ ክንውን
የሚረዳቸው
ግለሰብና፣ አንድ
ሴክሬተሪ ቀጥረው
ስራቸውን በቅርቡ
ይጀምራሉ።
የተከራዩት
ቢሮ ስምንት ክፍሎችና
አንድ ሽንት ቤት
ሲኖሩት
ከኮምፒዩተሮችና
ሌላም ኤሌክትሮኒስ
ነክ ከሆኑ እቃዎች
በቀር ለስራ
የሚያስፈልጉ እቃዎች
ሁሉ ተሟልተዋል።
እነዚህንም
ኮምፒዩተሮችና
ለኔትወርክ
የሚያስፈልጉ
ቁሳቁሶች አስመልክቶ
በኮንትራት የቀጠሩት
ኮንስልታንት የበለጠ
ስለሚያውቅ
የሚፈለገውን በጀት
ከሱጋር ሆነው
ለመመደብ ሲሉ ነው።
በነገራችን ላይ ይህ
ኮምፒዩተር አማካሪ
(Consultant) ስሙ አቶ ለጋሱ
ይባላል። ብዙ
ኔትዎርኮችን
ሰርቶዋል፣
ኮምፒዩተር ግዥም
በተለያዩ
መስሪያቤቶች
እረድቶዋል። አቶ
አደፍርስ
ኮምፒዩተሮቹ
መሟላታቸው አጣዳፊ
እንደሆነ
ተገንዝበዋል። ምንም
እንኳን ስራ ገና
ባይጀምሩም ጊዜው
መድረሱ አይቀርምና
ሁሉ ነገር በተቀላጠፈ
መንገድ ጊዜ ሳይፈጅ
መጠናቀቅ
እንዳለበትም
ተረድተዋል።
ስለዚህም ቢሮዋቸው
ከለጋሱ ጋር ሆነው
ፕላን ማድረግ
አስፈላጊ መሆኑን
ስላመኑበትና ስራዎች
በምን መልክ
እንደሚሰሩ አንዳንድ
እቅድም ስላላቸው፣
ለዚህም በቂ ጊዜ
መድበዋል።
አቶ
አድፍርስ ሞባይል
ቴሌፎናቸውን
አውጥተው አቶ ለጋሱ
ሞብል ቴሌፎን ከደወሉ
በኋላ፣
በኮምፒዩተሮቹ ሁኔታ
ላይ ቢሯቸው በነጋታው
ተገናኝተው ዝርዝር
ሁኔታውን
እንዲነጋገሩበት
አሳሰቡት።
በነጋታውም
በተባለው ሰአት ለጋሱ
ቢሮዋቸው ተገኘ፤
የሚገባውን ሰላምታ
ለአቶ አደፍርስ
ካቀረበ በኋላ ከፊት
ለፊታቸው ለእንግዳ
የተዘጋጀውን ወንበር
ጎተት በማድረግ
ተቀመጠ። እሳቸውም
ትሁት የሆነ ሰላምታ
መለሱለት። አቶ ለጋሱ
የተለያዩ
ኮንሳልቴሽን
ለመስጠት
በሚሄድባቸው ቦታዎች
ሁሉ ላፕቶፑን
የስብሰባ
መነጋገሪያዎችና
የተለያዩ
ፕሬዘንቴሽን
ለማቅረብ
ይጠቀምበታል። ከአቶ
አደፍርስም ጋር
የተለየ አልነበርምና
ላፕቶፑን በማውጣት
የስራ መመሪያ
ለመቀበል ዝግጁ ሆኖ
ቀረበ።
|
|
አቶ
አደፍርስ
ንግግራቸውን
በመጀመር፣ አቶ ለጋሱ
በሚሉበት ሰአት
ድምጻቸው ጎርነን
ስላለ ጉሮሮዋቸውን
ካሰሉ በኋላ
በመቀጠል፣
እንድንገናኝ ዋናው
የጠራሁህ
የኮምፒዩተር
አቀማመጦችንና የስራ
አሰላለፍን
በሚመለከት አንዳንድ
መመሪያዎችን ልሰጥህ
ስለፈለግሁ ነውና
እነዚህን በዋነኛነት
አስቀምጣቸው ብለው
የሚፈልጉትንም
ሲዘረዝሩ በሚከተሉት
ያስቀምጡታል።
- በኮምፒዩተር
የሚሰሩ ስራዎች በሙሉ
ማለትም አካውንቲንግ
በራሱ ዘርፍ፣
ማርኬቲንግም እንዲሁ
መሆን አለበት።
ወደፊት በየፊናቸው
እድገት ካለ
የየራሳቸው ቡድን
ለማዘርጋት እንዲረዳ
መሆን አለበት።
- ኢሜይልና
ኢንተርኔት አክሰስ
ማድረግ አስፈላጊ
ነው። ከቢዝነስ
ክላይንቶቻችንና
ወደፊትም ለሚመጡ
ቢዝነሶች፣ ብሎም
እርስ በርስ ሳንገናኝ
ከሰነበትን በኢሜል
ለመቀያየር
ያስችለናል።
- ኢሜይል አጠቃቀምን
በሚመለከት፣ ከቢሮ
ማይክሮሶፍት
አውትሉክን፣ ከቢሮ
ውጪ ደሞ ብራውዘር
መጠቀም እንዲቻል
መሆን አለበት።
- ሁሉም ሰራተኞች
በጋራ
የሚጠቀሙባቸውን
ስራዎች አንድላይ
እንዲቀመጡ
እፈልጋለሁ።
- ከዚህ ሌላ አንዱ
የሌላውን የግል ስራ
አስመልክቶ በጭራሽ
አክሰስ እንዲኖረው
መደረግ የለበትም።
አካውንቲንግ የራሱ
የተለየ ቦታ እንዲሁም
ማርኬቲንግ። ለኔም
የተለየና ማንም
አክሰስ የማያደርገው
ቦታ ታዘጋጅልኛለህ።
- የሁሉንም ስራ ማየት
የሚችለው እኔ ብቻ ሆኖ
መዘጋጀት አለበት።
- ስራችንን ማንም
ከውጪ ጠልፎ ማየት
እንዳይችል መደረግ
አለበት።
- ፕሪንተርን
በሚመለከት፣ ለአሁኑ
አንድ ጥራት ያለውና
ሁላችንንም
ሊያገለግል የሚችል
ፕሪንተር
ታስተካክልልናለህ።
- አንድ ፋክስ ማሽን
ያስፈልገናል፣ ሆንም
የሚመጡ ፋክሶችም ሆነ
የሚላኩ በኢሜላችን
አማካኝነት
ለተላከለት ግለሰብ
መድረስ እንዲችል
ቢሆን ይመረጣል፣
ነገር ግን አንገብጋቢ
አይደለም። ቢያንስ
በፕሪንት መልክ
ፋክሶችን ማግኘት
መቻል አለብን።
ስለዚህም ይህንን
ፋክስ ሁላችንም በጋራ
መገልገል እንድንችል
መሆን አለበት።
አንዳንዴ
የምንጠቀምበት ሁኔታ
ይኖራል ብዬ
እገምታለሁ፣
ከተለያዩ መ/ቤቶች ጋር
ለምናደርገው ደብዳቤ
ልውውጥም ማስፈለጉ
አይቀርም።
- የተሟላ
የማይክሮሶፍት ኦፊስ
ሶፍትዌር ሊኖረን
ይገባል።
- ከዚህም ሌላ
ለአካውንቲንግ
የሚረዱ የታወቁ
ሶፍትዌሮችም ካሉ
ወደፊት ልታጠናቸው
ይገባል። አሁን ብዙ
ወጪ ስላለ
የሚያስፈልጉ
የአካውንቲንግ
ተግባሮችን
ማይክሮሶፍት
ኤክስኤልንና
አክሰስን መጠቀም
እንዲቻል የተለያዩ
የአሰራር አይነቶችን
የሚጠቁሙ (ወይም templates)
ብታስቀምጥልን
የበለጠ የተቀላጠፈ
ስራን መስራት
ይቻላል። ወደፊት ግን
የበለጠ በጀት
አዘጋጅቼ
የአካውንቲንግ ስራን
የሚረዳ ሶፍትዌር
እንድታዘጋጅልን
ይሆናል።
- ለአሁኑ
ስራችንን ለመጀመር
የሚጠቅሙን እነዚህ
ናቸው ብዬ አምናለሁና
እነዚህን ለማካሄድ
የሚፈጀውን ወጪ
አጥንተህ ባፋጣን
እንድትነግረኝ
እፈልጋለሁ
የቀጠርኳቸው
ሰራተኞች ስራቸውን
ከመጀመራቸው በፊት
ይህ ሁሉ መጠናቀቁ
ሁላችንንም ምርታዊ
እንድንሆን
ያደርገናል ካሉ
በኋላ፣
|
|
|
|
በኔ
በኩል ይህ ነው
ጨርሼያለሁ ጥያቄዎች
አሉህ ወይም ግልጽ
ያልሆነ ነገር አለወይ
ብለው ጠየቁ። አቶ
ለጋሱም፣ ሁሉ ነገር
ግልጽና ሊሰራ የሚችል
ነው ብሎ
ካረጋገጠላቸው በኋላ
በጥሩ ፕላን ለመስራት
ቢሮዎቹ የፍሎር ፕላን
(የመሬት ፕላን)
አላቸው ወይ?
የዚህንስ ህንጻ
የጥገና ክፍል (facility)
ሃላፋ ማየት ይቻላል
ወይ? ብሎ ከጠየቀ
በኋላ ሲያብራራ፣ ሁሉ
ነገር ጥራት ባለው
መልክ ለመስራትና
ለምንሰራው
የሚያስፈልጉ
መዋቅሮች ያሉበትንና
ወደፊት ችግሮች
ሲከሰቱ
የምንጎበኛቸው
መዋቅሮች ሁሉ ለይቶ
ማወቅ አስፈላጊ ነው
ካለ በኋላ በመቀጠል፣
ስለዚህም በፍሎር
ፕላኑ ላይ ያሉትን
መሰረት በማድረግ፣
ወደፊት የሚጨመሩትን
የኔትወርክና ለዚሁ
አስፈላጊ መዋቅሮች
የሚሆኑ ሲጨመር ከጊዜ
ወደጊዜ በፕላኑ ላይ
በማስፈር ውጤታም
የሆነና ለማንም ግልጽ
የሆነ አሰራር
በማስፈር ፕላኑን
የሚመለከት በቀላሉ
መረዳት ይችላል ብሎ
አብራራላቸው።
እሳቸውም ሲከራዩ
የሰጡዋቸውን
የህንጻው አመራሮች
ቁጥር ፋይል
ያደረጉበትን
በማውጣት፣ ታዲያ
ለምን አሁኑኑ
አንጨርሰውም
ከመሄድህ በፊት
በማለት ስልክ ደውለው
የጥገና ክፍል
(ፋሲሊቲ) ሃላፊው
ቢሮዋቸው መሆናቸውን
ካረጋገጡ በኋላ ፈገግ
እያሉ፣ እኔም ከቢሮ
ልውጣ፣ አሁን
የማደርገው ነገር
ይህን ያህል የለምና
እግረመንገዴን ወደ
ጥገና ክፍል ሃላፊው
ልውስድህ ብለውት
አብረውት ወጡ።
እዚያም
ሲደርሱ አቶ አደፍርስ
ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ
ይህ ኔትወርኬን
የሚሰራልኝ
ኮንሳልታንት ነውና፣
የቢሮዬን የመሬት
ፕላንና (floor plan) ሌላም
ለኔትወርክ ግንባታ
የሚፈልጋቸውን
ነገሮች እናንተ
በምትፈቅዱት መሰረት
ማግኘት እንዲችል
ፈቅጄለታለሁና
የሚፈልጋቸውን
ነገሮች ተባበሩት ካሉ
በኋላ በሉ መልካም ጊዜ
ብለው ወጡ። አቶ
ለጋሱም የሚፈልገውን
ፍሎር ፕላን ጠይቆ
ካገኘ በኋላ
አመስግናለሁ፣
ወደፊት የምፈልጋቸው
ነገሮች ካሉ ብቅ
እላለሁ ብሎ ከጥገና
ክፍል (facility) ሃላፊው ቢሮ
ወጣ። አቶ ለጋሱ
የቢሮዎቹን አቀማመጥ
በመመልከት የፍሎር
ፕላን ማውጣት
ይችላል፣ ከዚህ በፊት
ተመሳሳይ ድርጊቶችን
ሰርቷል። ነገር ግን
ትልቅ ህጻ ሲሆን
በጣራው (conduit) ውስጥ
የሚሳቡ ኬብሎችንና
ወደዋናው መስመር
የሚሄድበትን፣ ጥሩ
ፕላን ከሆነ፣ የት
እንደሚኖር በተሻለ
ስለሚያሳይ በግምት
ከመራመድ የተረጋገጠ
ፕላን ይዞ ለመጓዝ
ይረዳል ብሎ
ስለሚያምን ነው።
ኔትወርክ
ግንባታ ንድፈ-ሃሳብ
አቶ
ለጋሱ አስፈላጊውን
ጥናቶች ደረጃ በደረጃ
መመልከት ጀምሮዋል።
አሁን ማካሄድ ያለበት
ኢንፎርሜይሽን
ስብሰባ እንደሆነም
ያምናል። ባጠቃላይ
ሁኔታውንም ሲገመግም
አቶ አደፍርስ
የጀመሩት ቢዝነስ
እያደገና በርካታ
ሰራተኞችን
የሚጨምሩበት
አጋጣሚዎች እንዳሉ
ነው የተገነዘበው።
ስለዚህ በቅድሚያ
የነገሩትን መሰረት
በማድረግ የተሟላ
ኔትወርክ መትከል ግቡ
ነው። ይህንንም
ለማድረግ ከጥገና
ክፍል ሃላፊው ባገኘው
ፕላን (የቢሮ ካርታ)
በተቀላጠፈ መንገድ
የቢሮውን ክፍሎች
ለነሱ በሚጠቅም መልክ
ማፕ ካደረገ በኋላ
በክፍሉ የሚገኙትን
የቴሌፎን መገናኛዎች
(faceplate) በሚገባ
ለማስቀመጥ እቅድ
አወጣ። ይህንንም ሁሉ
ለማድረግ አቶ ለጋሱ
የሚከተሉትን ነደፈ።
- ዳያላፕ
ግንኙነት ወይስ ብሮድ
ባንድ? ከዋጋ አንጻር
ዳያላፕ ተወዳዳሪ
አይገኝለትም፣ ሆኖም
የመጨረሻ ዳውንሎድ
ፍጥነቱ 56kb/s ሲሆን፣
ይህንን ግንኙነት
ከተጠቀምኩ አራቱም
ሰራቸኞች፣ አቶ
አደፍርስን ጨምሮ፣
ይህንን ግንኙነት ነው
የሚጋሩት። ዳያላፕን
መጋራት አዲስ አበባ
ውስጥ የተለመደ
አሰራር ነው። ስለዚህ
ትልቁ የስራ ክንውን
በኢንተርኔት ላይ
ስላልሆነ፣ አሁን
ባለው የስራ ሃይልና
መጠነኛ ኢንተርኔት
አጠቃቀም የሚታይ
ችግር አይኖርም።
ነገርግን ብሮድባንድ
ከሆነ ከፍጥነቱ ጋር
ክፍያው እያደገ
ይሄዳል፣ ከዳያላፕ
ጋርም ሲነጻጸር
በትልቅ ደረጃ
ይለያያሉ። ፍጥነቱ
ወደር ባይኖረውም
ዋጋው ግን እጅግ በጣም
ውድ ነው። በአገራዊ
አሰራር ፖሊሲዎችም
ሳቢያ ምርጫችን ውሱን
ነው። እነዚህን ሁሉ
መርምሬ ለመጀመሪያ
በዳያላፕ ኔትወርክ
ላይ አተኩራለሁ።
ስለዚህም ተስፋ
ኢንኮርፖሬሽን ባለው
መጠነኛ የኢንተርኔት
ግልጋሎት አንጻር
የዳያላፕ ግንኙነት
በቂ እንደሆነ መገመት
አያዳግትም።
ስለዚህም ወደፊት
አስፈልጊነቱ እየጎላ
መጥቶ ብሮድባንድ
ኢንተርኔት ሲገባ
በኔትወርካችን
መዋቅር
ላይ፣ ከፍጥነት
በቀር፣ ምንም
አይነትን ለውጥ
በማያመጣ መልክ አሁን
የምናስገባውን
የኢንተርኔት
ግንኙነት መገንባት
ይኖርበታል። ለዚሁም
አገልግሎት
ከኢንተርኔት
ለሚኖረው ግንኙነት
በአምስቱ
ኮምፒዩተሮች ስም ሆኖ
ግንኙነትን
የሚፈጥር(ወይም NAT-Network Address
Translation) አይነተኛ
የአሰራር ዘዴ ነው
ነው። ይህም ከዳያላፕ
ግንኙነታችን
የሚመጣው ሲግናል
በኔትወርክ ኬብል
አማካኝነት በየክፍሉ
ያሉ ኮምፒዩተሮች
በጋራ ለመካፈል
የሚችሉበትን ሁኔታ
መፍጠር ያስችለናል።
|
|
- ፍላጎቴ በርካታ ኮምፒዩተሮች
በጋራ የኢንተርኔትን
ትራፊክ መጋራት
እንዲችሉ ማድረግ
ሲሆን፣ ከዚሁም ጋር
የሎካል ኔትወርኩን
ትራፊክ ከኢንተርኔት
ትራፊክ ማስክ ማድረግ
መቻል ይሆናል።
ስለዚህ ከኢንተርኔት
ጋር ያለ ግንኙነት
ዳያላፕ ይሆናል። ይህ
ተግባር የበለጠ
ወደመጠረሻው
የምንሰራው ተግባር
በዚሁ አቆማለሁ።
- ዳያላፕ ግንኙነታችን ቋሚ
የቴሌፎን መስመር
ያስፈልገዋል ብዬ
አምናለሁ፣ ስለዚህም
ለሱ ብቻ አንድ ቴሌፎን
መስመር እናዘጋጃለን።
ወደፊት የብሮድባንድ
ምርጫዎች ካሉን፣
ምናልባት ዲ.ኤስ.ኤል
ሊሆን ይችላል። ከዚህ
ሌላ ብዙም የብሮድባንድ
ምርጫዎች የኢንተርኔት ሰርቪሱ
የሚሰጥ አይመስለኝም፣
ለምሳሌም ቲ1፣
ዲ.ኤስ1፣ ፍሬምሪሌይ፣
ኦፕቲካል ቻናል እና
የመሳሰሉት።
ስለዚህም ዲ.ኤስ.ኤል
የሚጠቀመው የቴሌፎን
መስመር ስለሆነ
የነበረውን የቴሌፎን
ቁጥር እንዳለ
እንጠብቀዋለን።
- ሌላው የድምጽ
ቴሌፎን መስመሮችን
በሚመለከት ምን ያህል
መስመሮች ያስፈልጋሉ?
ከዚህስ ጋር ወደፊት
እድገት ሲጨምሩ
በፍጥነት መስመር
መጨመር የሚቻልበትስ
ሁኔታ አለ ወይ
የሚለውን ለመመለስ
የቴሌን አሰራር በዚህ
መልክ ምን እንደሆነ
ከቴሌ ማጣራት። ምንም
እንኳን የቴሌፎን
መስመሩን በሚመለከት
የቢዝነስ
ስምምነታችን ውስጥ
ሙሉ በሙሉ
ባይሰፍርም፣ አብሮ
መስመር እንዲይዝ
ማድረጉ በመጠኑም
ስምምነታችን ላይ
አስፍረነዋል። ሌላው
ግን አቶ አደፍርስ
መልካምና ለጋስ ሰው
ናቸው።
ኮንትራታችንን
ስንጀምር የኔን ክፍያ
አስመልክቶ
በጠየቅሁት መሰረት
ነው ካለማወላወል
የተስማሙት፣ ነገር
ግን ጥራት ያለው ስራ
እፈልጋለሁ የሚለው
ቃል ማነኛውንም የስራ
መመሪያ ሲሰጡ
የማይለይ ቃላቸው
ነውና በስራው
እንዲደስቱ
እፈልጋለሁ፣
ወደፊትም ማን ያውቃል
ትልቅ መ/ቤት ሆኖ
ኔትወርካቸውን ከላይ
ሆኜ
እንድቆጣጠርላቸው
ይሰጡኝ ይሆናል በዬ
አምናለሁ። ከዚህም
ሌላ የሳቸው ውጤታም
መሆን ለኔ
ኮንሳልቴሽን ስራ
መሳካት ትልቅ
አስተዋጽኦ አለው።
<
>
- ከኢንተርኔቱ
ቴሌፎን መስመር ሌላ
ወደፊት በተፈለገ ጊዜ
ማደግ የሚችል፣
ለጊዜው አምስት
ሮልኦቨር ቴሌፎን
መስመሮች (ለምን ሮል
ኦቨር አስፈለገ?
በቀላሉ ማናጅ ማድረግ
ያስችላል። ብሎም ቢሮ
ውስጥ ሰው ሳይኖር
የሚፈለገውን መልክት
ለመተው እንዲያመች፣
ወደሚፈለገው ቢሮ
መስመር መፍቀድ
እንዲቻልና የተለያዩ
ጥልቀት ያላቸው
የቴሌፎን እድገቶችን
ለማድረግ ይረዳል)
ያስፈልጋሉ። ለሁሉም
ቴሌን በማነጋገርና
ያሉትን አማራጮች ሁሉ
መስመር ማስያዝ
ተቀዳሚ ተግባር ነው
ብዬ አምናለሁ።
- በፍሎር ፕላኑ
መሰረት ጠቅላላ
ክፎሎቹ 8 ናቸው፣
ሽንትቤቱን
ሳይጨምር። ምንም
እንኳን አንድ ነጻ
ክፍል ቢኖርም ለጊዜው
ያለን ኔትወርክ
በሚገባ
ያስተናግድልናል ብዬ
አምናለሁ። ስለዚህም
ለአሁኑ አምስት
የኔትወርክ
ተጠቃሚዎች ይኖራሉ።
- የሚዘረጉ
የኔትወርክ ኬብሎች
በሙሉ የሚገናኙት
ከቴሌፎኑ መገናኛ (faceplate)
ጋር ሲሆን፣ አሁን
ያለው የቴሌፎን
መገናኛ (faceplate)
የኔትወርክ ተጨማሪ
መስመር (ወይም ports)
የሉትም፣ ስለዚህም
በየቢሮው ግርግዳ ላይ
የተለጠፉትን አምስት
የቴሌፎን ማገናኛዎች
(faceplate) በሙሉ በአዲስና
እያንዳንዳቸው
ማገናኛዎች (faceplate) አንድ
የቴሌፎን መገናኛ (V)፣
አንድ የፋክስ (V2)ና
አንድ ደሞ ለኔትወርክ
(D)ፖርቶች
ያስፈልጉታል።
በድምሩ ሶስት
መስመሮች (ወይም ports)
ያሉት ማገናኛ ((faceplate)
ማድረግ ይኖርብኛል።
- ከትንሿ የቡና መጠጫ
ክፍል
ወደያንዳንዳቸው
ቢሮዎች የኔትወርኩ
ገመድ (cable) መዘርጋት
ይኖርበታል፣
የቴሌፎኑን ገመድ
በሚመለከት
የነበረውን ነው
የምንጠቀመው።
የተለየ የምናደርገው
ቢኖር፣ አዲሱ
የግርግዳው ማገናኛ
(faceplate) ጋር
እናስረዋለን።
- ኔትወርካችንን
ማናጅ የሚያደርግልን
አንድ በካስተም
የተሰራ የኔትወርክ
እቃዎቻችንን
የሚያስቀምጥልን
ግርግዳ ላይ የሚሰቀል
(ወይም wall mount rack)
ያስፈልገናል።
ተዘጋጅቶ ለሺያጭ
የቀረበ አዲስ አባባ
ውስጥ ስለሌለና
ከውጭም ማምጣት
ከጊዜና ከወጪ አንጻር
ጥሩ አማራጭ ስላልሆነ
ይህንን የኔትወርክ
ማናጅመንት እቃ (wall mount rack)
ብረታብረቶችን
ከሚሰሩ በካስተም
አሰራለሁ። ይህም
በአልሙነም የተሰራ
መሆን አለበት
ምክንያቱም ስታቲክ
ስለማይዝ ነው። ዋጋው
በትንሹ 400 ብር ወይም
በላይ ሊሆን ይችላል።
ይህንንም ለመገንባት
ስፐስፊኬሽን
ከአምሮዋችን
የምናመነጨው ሳይሆን
በወቅቱ ተቀባይነት
ያለውና ወደፊት
የተለያዩ እቃዎችን፣
ለምሳሌም ራውተርና
ሌላም ስንጨምር
ስታንደርዳይዝድ
የሆነ rack ስለሆነ
ካለችግር ቦታ
ይይዙልናል።
- ባገኘሁት
ፍሎር ፕላን ላይ
የሚከተሉትን
በመጨመር አዲሱ
የፍሎር ፕላናችን
ስእል 1.0 ን ይመስላል።
አዲሱ የኬብል
ማገናኛችን (ወይም faceplate)
እንደሚታየው ቦታ
ቦታቸውን ይይዛሉ።
|
|
|
|
ስእል
1.0
የተሻሻለ የቢሮ
ፍሎር ፕላን
- ሁሉን ባንድነት
አጣምሮ የያዘ
ፕሪንተር - ፋክስ፣
ኮፒና ፕሪንቲንግ
ያለው ሁለገብ
ፕሪንተር ከገዛን
የሚመጣውን ፋክስ
በቀጥታ በፕሪንቲንግ
መልክ ማግኘት
ይቻላል።
- ኢሜይልን
በሚመለከት
ኢንተርኔት ሰርቪሱ
ለአንድ ዳያላፕ
አካውንት አንድ
ኢሜይል አካውንት ብቻ
ስለሆነ የሚፈቅደው፣
አስፈላጊ ሆኖ ከአዲስ
አበባ ውጭ የስራ ጉዞ
የሚያደርጉበት ሁኔታ
ካለ፣ ቢያንስ አቶ
አደፍርስ ማድረጋቸው
ስለማይቀር፣ ተጨማሪ
ኢሜይል አካውንት
አስፈላጊ ነው። አቶ
አደፍርስ ባወጡት
መመሪያ መሰረት
ከቢሮና ከውጪም
ኢሜይል አክሰስ
ማስቻልን ስለሚፈልጉ
አራት አካውንቶችን
ከዳያላፕ አካውንቱ
ጋር መፍጠር
ያስፈልጋል።
- ወደፊት
ቢዝነሳቸው እያደገ
ሲመጣና የጠለቀ
የኔትወርክ እድገት
የሚጠይቀን ደረጃ
ሲደረስግንባታችን
በዚያው መጠን
እየጨመረ መምጣቱ
እንደማይቀር
ተገንዝቤያለሁ።
አሁን ልሰራ ያቀድኩት
የኔትወርክ መዋቅር
ለመጪው ባይተዋር
እንዳይሆን፣
የኢንተርኔት
ግንኙነታችን ስፋት
(Bandwidth) እድገት ከፍጥነት
መጨመር በቀር በምንም
አይነት አሁን
የሰራነው ኔትወርክ
ወደፊት በሚመጣው ላይ
ተጽእኖ ማድረግ
እንዳይኖርበት ሆኖ
መዋቀር አለበት።
ስለዚህ ወደፊት
የኢንተርኔት ፍጥነት
ሲጨምር ከሱጋር
የሚመጡ አዳዲስ
እቃዎች፣ ለምሳሌም
ራውተር ወይም ስዊችና
የመሳሰሉት እቃዎች
ከኢንተርኔት ጋር
የኔትወርክ
ግንኙነታችንን
ፍጥነት ለመጨመር
እንጂ የመዋቅር ለውጥ
ማድረግ
የሚያስገድደን ሁኔታ
ውስጥ መግባት
አይኖርብንም።
ስለዚህ የአሁኑ
ሲስተማችን ወዲያውኑ
ከፍጥነቱ ጋር እራሱን
ያስተካክላል
ካለምንም ለውጥ።
- አቶ
አደፍርስ ባሉት
መሰረት፣
እያንዳንዳቸው
የየግል ስራቸውን
የሚሰበሰቡበት፣
አካውንቲንግ በራሱ
ዘርፍ ማርኬቲንግም
እንዲሁ፣ ይህንን
ሊያሟላልን የሚችልና
ወደፊትም መካከለኛ
አልፎም ትልቅ
ኔትወርክ ግንባታ
ድረስ ሊዘልቅ
የሚችል፣ ብሎም
ደህንነቱ (Security)
አስተማማኝ የሆነ
የሊኒክስ ሰርቨር
ሲሆን ከዚሁም ጋር
የላይሰንስ ክፍያም
ሆነ የሶፍትዌር ወጪ
የለበትም። ስለዚህም
ከማይክሮሶፍት
ዊንዶውስ ሰርቨር
ይልቅ ሊኒክስ
ሰርቨርን ለኔትወርክ
ግንባታችን
እመርጣለሁ።
- በዚህም
ሰርቨር ላይ
የሚያስፈልጉ
ግልጋሎቶች
ፕሪኒቲንግ፣ ፋይል
መጋራት፣ የግል ሎጊን
ማድረጊያ ቦታና ፋይል
ማስቀመጫዎች ሲሆኑ
እነዚህን በሚገባ
የሚያስቀምጥልን
የሳንባ (samba) ሰርቨር
ይሆናል። ጥሩ ፕላኒግ
በማዘጋጀት ወደፊት
እያደገ ሲሄድና
ቅርንጫፍ መ/ቤቶች
ሊኖራቸው የሚችልበት
ሁኔታ ከተፈጠረ
በቀላሉ ከአንድ በላይ
የሆኑ ኔትወርኮችን
ለማገናኘት
የሚያስችሉ
ሰርቪሶችን
በግንባታችን ውስጥ
ሊኖር እንደሚችል
በመገመት መሰረታዊ
የሳንባን (PDC - Primary domain controller)
እገነባለሁ።
- በምንም አይነት
ስታንደርዳይዝድ
ያልሆነ የስራ ሂደት
በኔትወርካችን ላይ
መትከል አልፈልግም።
የአሁን እፎይታ
የበኋላ ውድቀትን (disaster)
ያስከትላልና።
|
|
ከሞላ
ጎደል እነዚህ
ቅጽበታዊ ግባችን
ናቸው። ቀጥሎም
ተግባራዊ ስራዎች
ናቸው የሚጠብቁን፣
ይህም ለዴስክቶፕና
ለሰርቨር የሚሆኑ
ኮምፒዩተሮችን፣
ፕሪንተር፣ ኔትወርክ
ኬብሎች፣ የቴሌፎን
ጃኮችና፣
የኔትወርካችን እቃ
ማናጅመንት ራክ ዋጋ
ማነጻጸር ይሆናል።
ይህም የነገ ቀኑን ሙሉ
ስራዬ አደረግሁት።
በነጋታውም
አዲስ አበባ የሚገኙ
የከምፒዩተር፣
ፕሪንተርና
ኤሌክትሮኒክስ
አስመጪዎችን ሁሉ
እየዞርኩ ጎበኘሁ።
ከዚሁ ጋር
የኔትወርካችንን ራክ
ከገመትነው ዋጋ ትንሽ
ከፍ ብሎ የሚሰራልንም
አገኘሁ፣
ሰርቨራችንን
በሚመለከት የተገነባ
ሳይሆን ብትን
እቃዎችን
የሚያቀርብልኝ
አገኘሁ። ፕሪንተርና
ዴስክቶፕ
ኮምፒዩተሮችንም
በጥሩ ዋጋ
የሚያቀርብልኝ
አገኘሁ፣ ኬብል
አስመጪዎች በመልካም
ዋጋ አጠቃላይ
ግንባታችንን
ለመጨረስ
የሚያስፈልገንን
ትክክለኛውንም ዋጋ
አወቅሁ። የዚህም
ኔትወርክ ኬብል
እርዝመት ከፍሎር
ፕላኑ በተወሰደ
መለኪያ መሰረት ነው።
ስለዚህም ከገመትነው
እርዝመት በመጠኑ ከፍ
አድርጌ ዋጋውን
አስገመትኩ።
የተሰበሰቡት
ኢንፎርሜይሽኖች
ማጠቃለያ
ይህ
ቻርት አቶ ለጋሱ
የኮምፒዩተር፣
የሰርቨርና ኔትወር
እቃዎች ዋጋ
ለማወዳደር
በዞረባቸው የተለያዩ
አከፋፋዮች መሰረት
አድረጎ ያጠናቀራቸው
ቻርቶች ናቸው።
ማሳሰቢያ፡
እነዚህ ዋጋዎች
ልበወለዳዊ ናቸው።
ትክክለኛው ዋጋ
በአዲስ አበባ ውስጥ
ከዚህ ሊበልጥ
ይችላል። ነገር ግን
ያንሳል ብዬ
አልገምትም።
ቻርት
1.0
ጠቅላላ
የኮምፒዩተርና
ኔትወርክ እቃዎችና
ዋጋቸው
|
| እቃው ስም |
መለያው |
አገልግሎቱ |
ዋጋው |
| ፕሪንተር/ፋክስ/ስካነር
|
ኤችፒ
#4609;ሉን የያዝ ሌዘር
ጥራት ያለው
ፕሪንተር
|
ፋክስ፣
ፕሪንተርና፣
ስካነር ባንድላይ
|
3600 ብር
|
| Network management rack |
Wall mount rack |
የኔትዎርክ
እቃዎች ማስቀመጫ
|
500 ብር |
| 5 ኮምፒዩተሮች |
ዴል
ኮምፒዩተር (2.4GHz፣ P4, 512MB RAM,
100GB h/d - 7200rpm, LAN onboard, multimedia, XP system
|
ዴስክቶፕ
ኮምፒዩተሮች፣
ሁሉም አንድ አይነት
|
22500 ብር |
| ሰርቨርኮምፒዩተር
|
እራሴየምገነባው (ቻርት 1.1)
|
|
13000 ብር |
| ኬብል(500 ft) |
Cat5 |
ፒሲከኔትወርክ
ለማገናኘት
|
|
| ራውቲንግ ሰርቨር |
ኢንተርኔት
ፒሲ ራውተር |
የቢሮ
ዳያላፕ ኔትወርክ
ራውተር
|
2700 ብር |
| ባለ 3 ፖርት 5 ፌስፕሌት
|
የኬብል መገናኛ |
የኬብልና
የቴሌፎን መገናኛ
|
|
|
ሰርቨሩንና
ኔትወርኩን
ለመገንባት
የሚከተሉትን
በጥንቃቄ መመልከት
ይኖርብኛል፡
- ለኔትወርኩ ማነቆ
(bottleneck) የሚሆነውን
በትክክል መለየት።
- የሊኒክስ ሰርቨርን
ለመገንባት ውሳኔ
ለምን እንዳደረግሁ
መጠነኛ ምክንያቶችን
ማቅረብ አስፈላጊ
ነው፣ ምንም እንኳን
በአለም ላይ ከ 75% በላይ
የሚሆነው ሰርቨር
ሊኒክስ ቢሆንም።
- ስኬለብሊቲን
በሚመለከት፡
የተጠቃሚው
የኔትወርክ አጠቃቀም
እየጨምረ ሲሄድና
አዳዲስ ኮምፒዩተሮች
በኔትወርኩ ላይ
እየተጨመሩ ሲመጡ
ሰርቨራችን ከጊዜ
ወደጊዜ የሚጠየቁ
ሰርቪሶችን
ካለምክንያት
መዝጋት፣ የሚጠየቁ
ኢንፎርሜይሽኖችን
ለማቅረብ ከሚፈለገው
በላይ መጎተትና፣
ሌላም ችግሮች መከሰት
ይጀምራሉ። ስለዚህ
ስኬለብሊቲ
ሰርቨራትን
ከኔትወርኩ እድገትና
አዳዲስ ቴትኖሎጂዎች
ሲመጡ አብሮ መሄድ
መቻልን፣ ብሎም
ችግሮች ሳይፈጠሩ
በፊት መቼ
ኔትወርካችን መጎተት
የሚጀምርበትን ሁኔታ
መተንበይ
ያስችለናል።
መሰረታዊው ተግባር
እዚህ ላይ
ኔትወርካችን
በተፈለገ ጊዜ ሁሉ
ግልጋሎቱን መስጠት
እንዲችል ማድረግ
ነው።
|
|
|
|
|
- ፐርፎርማንስን
በሚመለከት፡
የሰርቨር ክንውን
ቅልጥፍና መሰረት
የሚያደርገው ያሉት
ግልጋሎቶች (services)
በሚፈለጉበት ጊዜ
አገልግሎት ለመስጠት
መገኘታቸው ነው።
በሌላ በኩል ሰርቪሶች
ሁሌም ከተያዙ፣
ለሌሎች ጥቅም
አገልግሎት መስጠት
የሚገኙበት ጊዜ
መገመት አዳጋች
ይሆናል። ከዚሁም ጋር
የሲፒዩን ትኩረት
የሚጠይቁ ሰርቪሶች
ከበዙ በጣም ውጥረት
ላይ ይሆንና ለሌላው
አገልግሎት ምንም
ትኩረት አይኖረውም፣
ባጠቃላይም
በሲስተማችን ላይ
የስራ ውጥረት
እንዳይኖር
የኔትውርካችን
ግንባታ ይህንን ሁሉ
ችግር በማቃለል ላይ
የተመረኮዘ መሆን
አለበት። ወይም ይህ
ሁኔታ እንዲከሰት
ምክንያት የሚሆኑ
አጠቃቀሞችን
በጥንቃቄ መመልከት
ይኖርብናል።
- ተመሳሳይ
አገልግሎቶች
መኖራቸው የስራ
ድግግሞሽን (redundancy)
ይፈጥራል ብሎም
አላስፈላጊ የተግባር
ግጭትና የስራ ውጥረት
በሰርቨሩ ላይ
ይፈጥራ። ለምሳሌ
አፓቼ ዌብ ሰርቨርን
ከተጠቀምን፣
ኢንተርኔት
ኢንፎርሜይሽን
ሲስተምስ (IIS - Internet Information Services)
ን መጠቀሙ ትርጉም
የለውም። ከዚህ
አይነቱ የስራ
ድግግሞሽ በጣም
መጠንቀቅ አለብን።
ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ
የጎላ ነው።
- ነጠላ
ሰርቨርን
በሚመለከት፡
ኔትወርኩ እያደገ
ሲሄድ፣ አዲስ
ሰርቪሶችን
መጨመራችን
አይቀርም። የዚያ
ጊዜስ ሌላ ሰርቨር ነው
የምንገነባው ወይስ
ባለው ላይ ነው
እድገትን
የምንጨምረው
የሚለውን ሁሉ ካሁኑ
መልስ መስጠት
አለብን። በኛ
ኔትወርክ
እስከመጨረሻው አንድ
ሰርቨር ለመቀጠል
እቅድ አለኝ ለዚህም
ነው በቻርቶቼ ላይ
እነዚህን ሁሉ ልመልስ
የሞከርኩት። ይህም
ወጪን ብቻ ሳይሆን
የሚቀንስልን የስራ
መዝረክረክን ጭምር
ይሆናል። በደንብ
ዲዛይን የሆነ ነጠላ
ሰርቨር ሊከሰቱ
የሚችሉ ነገሮችን
በሙሉ በትክክል
ከተጠኑና በዚያ ላይ
የሆነ ግንባታ
ከተደረግ ሪሶርስ
ዩቲላይዜሽን፣
ፐርፎርማንስና፣
የተመጣጠነ ሰርቨር
እንደምንገነባ
ጥርጥር አይኖረውም።
ስለዚህ ይህንን ችግር
ካሁኑ መተንበይ መቻል
አለብኝ።
የሚከተሉት
ቻርቶች ይህንን
ነጥቦች በሚገባ
ይመልሱታ ብዬ
እገምታለሁ።
ቻርት
1.1
የሰርቨር
ቁሳቁሶቻችን
በዝርዝር
|
| ቁሳቁሶች |
ካፓሲቲ |
ፍጥነት |
አገልግሎት |
ካሽ |
ዋጋው በብር |
| Quad-Core Intel® Xeon® processors |
ሰርቨርና/ዴስክቶ
ክላስ |
1.6-3GHz ክሎክ ስፒድ |
ፕሮሰሰር |
4 MB L2 Cache |
ክ 2070 - 7785 |
| ሜሞሪ |
4GB |
60ms |
ሲስተም ሜሞሪ |
|
1800 |
| ሀርድ ድራይቭ |
500GB x 2 |
7200 RPM |
ኦግዝለሪ ሜሞሪ |
ውስጣዊ |
2 * 1350 |
| ሜይን ቦርድ፣ ስከዚ
ሲስተም |
|
|
ኢንቴልቺፕሴት |
1MB |
1800 |
| ፓወርሳፕላይ |
450 watts |
n/a |
ሀይልምንጭ |
N/a |
540 |
| ITX case |
n/a |
n/a |
n/a |
N/a |
1080 |
| ጠንካራ
ቬንትሌሽን ሲስተም
(Fan) |
ከፍተኛ
አየር ስርጭት/ዝቅተኛ
ድምጽ |
1200 – 1800 |
ማቀዝቀዣ(cooling) |
N/a |
400 |
| ሲፒዩፋን |
|
??RPM |
ሲፒዩማቀዝቀዣ |
n/a |
480 |
| ሞኒተር |
ቢናንስ 1024x768
ሪዞሉሽን |
ሪፍሬሽ ሳይክል |
ሞኒተር |
n/a |
630 |
| ማውስ |
n/a |
n/a |
ኪቦርድ |
n/a |
80 |
| ኤክስተርናል
ድራይሽ |
500GB |
7200 RPM |
ባካፕድራይቭ |
--- |
1500 |
| ኪቦርድ |
|
|
|
|
180 |
|
ይህንን
ሁሉ ካጠናቀርኩ በኋላ
ከአቶ አደፍርስ ጋር
ቁጭ ብለን ሁሉንም
አንዳ ባንድ
ተነጋገርን። በርካታ
ሰአቶች ስለሁኔታው
አጠፋን። ሁሉንም
በቀላሉ ሊገባ በሚችል
መልክ
አስቀመትኩላቸው።
የሚቀጥለው ደረጃ
እቃዎቹን መግዛት
ሲሆን አቶ አደፍርስ
ሁሉን ነገር
አዘጋጅተዋል። የኔ
ፕላን የኔትወርክና
የሰርቨር ግንባታዬን
በቀጥታ መጀመር ነው።
ለነገሩ ብዙም
የሚያጣድፍ ነገር
የለም ምክንያቱም ስራ
ለመጀመር ሳምንታቶች
አሉና። ነገር ግን
ቀደም ብሎ ተዘጋጅቶ
መጠበቅ ደሞ ይጠቅማል
እንጂ አይጎዳም። ማን
ያውቃል፣ መጨረሻው
ላይ ሰይጣን
በመንገዳችን ላይ
ይሆንና በስማም ወልድ
ማለት ከማያውቁትን
እርዳታ እንደመጠየቅ
ይሆናል። በቀኝ
አውለኝ ብለን ከወጣን
መንግዳችን ከሰይጣን
የጸዳ ይሆናል።
ሀሌሉያ እላለሁ! አሜን
በማለት ተባበሩኝ
እንጂ? ይቅርታ
ሃይማኖት አስተማሪ
ለመሆን ሳይሆን
መጨረሻው ላይ ለስራ
መጣደፍ የሚመጣው
ነገር አይታወቅምና
ሁሉ ጊዜ በቂ ጊዜ
መስጠት አስፈላጊ ነው
ለማለነው።
ሁሉን
ነገር የተበታተነ
ስለምገዛ አንዳንዶቹ
እቃዎች
የሚያገናኛቸው እቃ
ያስፈልጋል።
ለምሳሌም ኬብሉን
ከኮኔክተሩ ጋር
ለማገናኘት Modular
plug crimp ያስፈልጋል፣ ፓች
ፓናሉና ፌስፕሌቶቹ
ላይ ዴብሉን
ለማገናኘት 110
ፓንችዳውን ከተር
ያስፈልጋል። እነዚህ
በትንሹ ለመጥቀስ
ነው።
|
|
|
የኔትወርክና
የኮምፒዩተር ቁሳቁስ
ስብሰባና ግንባታ
በነጋታው
ጠዋት ተነስቼ ባለፈው
የጎበኘኋቸውን
የኮምፒዩተርና
የኔትወርክ እቃ
አቅራቢዎች
በተነጋገርነው
መሰረት እቃዎቹን
ለመግዛት ጎዞየን
ወደዚያው አመራሁ።
ባለፈው
በጎበኘሁበት ጊዜ
ዋጋቸውንና
ጥራታቸውን
በሚመለከት ቢያንስ
ከሚቀጥለው 5 አመታት
በፊት ኮምፒዩተሮቹ
ሳይቀየሩ
የሚሰሩበትን ይዘት
ሁሉ ገምግሜያለሁ፣
የሚቀረው
የተነጋገርንበትን
ክፍያ አጠናቆ
ኮምፒዩተሮቹን
እንዲልኩልኝ ማድረግ
ነው።
እንደደረስኩም
ሰላምታየን
ለሰራተናው ካቀረብኩ
በኋላ፣ ባለፈው
እንደተነጋገርነው
አምስቱን
ኮምፒዩተሮችና
ለሰርቨር
የተበታተነውን
የኮምፑተር እቃዎች
በጠየቅሁት መሰረት
ክፍያውን ልከፍልና
ቦታው ላይ
እንድትልኩልኝ
ለመጨረስ ነው
የመጣሁት።
ሰራተኛውም
ጥሩ አቀባበል ካደረገ
በኋላ ወደገንዘብ
ተቀባዩ እያመራው
ለክፍያው እዚያ ክፍል
ሄደው ያጠናቁ ካለው
በኋላ ትንሽ አብሮት
እንደመሄድ ብሎ
አቅጣጫውን እንደያዘ
ስለገባው
ኮምፒዩተሮችን
ሊያዘጋጅ ወደ እቃ
ማከማቻ ክፍል ገባ።
አቶ
ለጋሱ ጨርሶ ሲወጣ
ሁሉን ነገር
አዘጋጅተው አሳዩት።
ከዚያም ከቦታው ሰው
መኖሩን ለማረጋገጥ
ጠየቁት፣ እሱም እኔ
እራሴ እዚያው
እኖራልሁ። እናንተ
ጭናችህ እስክትጨርሱ
እዚያው ቀድሜያችሁ
እደርሳለሁ ካለ
በኋላ፣ እዚያው
እንገናኝ ብሎ ወጣ።
እንዳለውም
በቀጥታ ወደ አዲሱ
መ/ቤቱ አመራ
እንደደረሰም
ክፍሎቹን አንድ ባንድ
መጎብኘት ላይ እንዳለ
እቃ አቅራቢዎች
መምጣታቸውን በድምጽ
አወቀና ሄዶ የዋናውን
የቢሮ በር
ከፈተላቸው።
አመላልሰውም ከጨርሱ
በኋላ አቶ ለጋሱ
ለሰዎቹ ጉርሻ ቢጤ
ሰጣቸው።
አሁን
የሚቀጥለው የቀሩትን
ኔትዎርክ - ራክ፣
ኬብሎችንና ሌላም
እቃዎች በሚመለከት
ከአስመጪዎች ጋ ሄዶ
ገንዘባቸውን
እየከፈለ እራሱ
ሊያደርሳቸው
የሚችላቸውን
በመኪናው እየጫነና
መላክ ያለበትን
አድራሻ በመስጠት
የሚፈለጉትን እቃዎች
ሁሉ በማጠናቀቅ
አሳለፈ።
አሁን
የሚቀረው ስራውን
መጀመር ሲሆን
ይህንንም ክንውን
ለማካሄድ በነጋታውም
ጠዋት ጀምሮ ቢያንስ
የኔትወርኩን ስራ
እስከሚችለው ድረስ
ለማገባደድ ሲሆን፣
በሚቀጥሉት ሶስት
ቀናት ውጥ ሁሉንም
ነገር መጨረስ
እንዳለብኝ እምነት
አድርጋለሁ። ግርግዳ
ላይ የሚቀመጠው
ቦርድና wall mount rack የሚላከው
ነገ ከሰአት አካባቢ
ሲሆን ይህ እቃ
የኔትወርክ
እቃዎቻችንን ማናጅ
ያደርግልናል።
ስለዚህ በፕላናችን
መሰረት የሚከተሉትን
እቃዎች ገዛሁ።
ምንድናቸው
የሚያስፈልጉ
የኔትወርክ ቁሳቁሶች?
- 110 ፓች-ፓናል።
አገልግሎት ከየቢሮው
የሚመጡትን ኬብሎችና
ከሞደሙ የሚመጡትን
ፓች ኬብሎች (በስእል 1.3
ላይ እንደሚታየው)
ማገናኘት ይሆና።
- ቢሮዎች ውስት አሁን
ያሉት የቴሌፎን
መገናኛ (faceplate) ባለአንድ
ፖርት ብቻ ናቸው።
እቅዴ ባል 3 ፖርት faceplate
ማስቀመጥ ሲሆን፣
ሁለቱ የቴሌፎን
መስመሮች (voice/fax) ና አንዱ
የዳታ መገናኛ (data port)
ናቸው።
- ማገናኛዎቹን
በሚመለከት፣ ለዳታ
ፖርት RJ45 connector - EIA/TIA 568B
ስታንደርድ መገናኛ
ሲሆን ለቴሌፎን ደሞ RJ11
connector ይሆናል።
የሚመከረው
ስታንደርድ EIA/TIA 568A
ሲሆን፣ ኢንዱስትሪ
በብዛት የሚጠቀምበት
ግም EIA/TIA 568B ነው።
ልዩነታቸው ስምንቱ
ኮፐር ሽቦዎች
ከአገናኝው ሶኬት ጋር
የተገናኙበት
አሰላለፍ ነው።
ለምሳሌም 568B ላይ፣
ጥንድ (ወይም pair) 2
በኮኔክተሩ ላይ
የሚይዙት ሰልፍ [1,2]
ሲሆኑ አይነታቸው፡ 1.white
with orange እና 2.orange with white ናቸው።
ተመሳሳይ የጃኬት
ከለር ያላቸው ሽቦዎች
የሚያያዙት በ 568A ላይ [3,6]
ረድብ ላይ ይሆናል።
ይህ ነው መሰረታዊ
ልዩነታቸው በ 568A እና 568B
መካከል። ጠለቅ ብሎ
ለማየት ካስፈለገ
ስለዋየሪንግ
አቀማመጥ በጥልቀት
የተጻፉ መጽሃፍቶችን
መመልከት
ያስፈልጋል፣ ወይም
መጠነኛ
ኢንፎርሜይሽኖች
በኢንተርኔት ላይ
ይገኛል እነሱን
መጎብኘት ነው።
ለማንኛውም
የዋየሪንግ አሰራርን
በሚመለከት ቴሌና
የመብራት ሀይል
ካወጡት መመሪያ ጋር
ግጭት ላለመፍተር
ጥንቃቄ መውሰድ
ያስፈልጋል።
የሁለቱን (A እና B)
ኬብሊንግ
እንዳታዋህዱት፣
ኔትወርካችሁ ሊሰራ
አይችልም።
- ማሳሰቢያ፡
ከዚህ በፊት ልምድ
ከሌላችሁ ተዘጋጅቶ
የተቀመጠ ኬብል
ስለሚኖር እሱን
መግዛት ይመረጣል፣
በተጨማሪም ፓች
ፓናሉም ስለሚኖርና
እሱን ተርምኔት
ማድረግ እውቀት/ልምድ
ስለሚጠይቅ ከዚህ
በፊት የስራ ልምዱ
ከሌለ ለሌላ ሰው
መስጠቱ አወዛጋቢ
የሌለው ምርጫ ነው።
|
|
|
|
|
|
ቀጥለንም
ከኮርኒሱ
ወደየቢሮዎቹ
ኬብሎችን ከህንጻው
ጋር ለቴሌፎን
በተዘጋጀው ትቦ ውስጥ
በማሳለፍ ለቴሌፎን
በተዘጋጀው ቦታ ላይ
አወጣን። በነገራችን
ላይ የቴሌፎን መገናኛ
(faceplate) ከሁሉም ክፍሎች
አውልቀናቸዋል
ምክንያቱም በአዲሱ
መቀየር አለብን።
ሁሉም
ክፍሎች የኔትወርክ
ኬብሉ ከደረሳቸው
በኋላ አዲስ በገዛነው
faceplate ላይ የቴሌፎኑንና
የኔትወርክ
ኬብላችንን
እናስራለን (ወይም punchdown
እናደርጋቸዋለን) ።
አሁን አምስቱንም
ክፍሎች ጨርሰናል፣
ቀጥለን ኔትወርክ
ክፍሉ በመመለስ ከፓች
ፓናሉ ወደ ሞደሙ
በተዘጋጀው ሶስት ፊት
(3ft) ፓች ኬብል አምስቱን
ክፍሎች
እናገናኛለን። አንድ
ክፍል ለጊዜው ሰው
አይኖርበትም፣ ነገር
ግን ተዘጋጅቶ መቀመጡ
አይጎዳም። ቀጥሎም
እያንዳንዳቸውን
ክፍሎች በመሳሪያ
የኔትወርኩን መኖር (Network
continuity) እንለካለን።
መሳሪያው(Network continuity tester)
አረንጓዴ ካሳየን ሁሉ
ነገር በደንብ
ተሰርቶዋል ማለት
ነው። አለዚያ ችግር
አለ። ይህንን
ለመለካት
ከያንዳንዳቸው
ቢሮዎች እየሄድን
የኬብሉን አንድ ጫፍ
ከሰራነው የኔትወርክ
ማገናኛ(faceplate) ላይ
እንሰካና የኬብሉን
ሌላውን ጫፍ ደሞ
በቴስት መሳሪያው ላይ
ስንሰካው አረንጓዴ
ከበራልን ሁሉ ነገር
በትክክል ተሰርቷል
ማለት ነው። ይህንንም
አደረግን፣ ሁሉም
ክፍሎች ግንኙነታቸው
ትክክል መሆኑን
አረጋገጥን።
እስካሁን
የሰራሁትን እስቲ
ላጠቃላቸው፡
- ራኩን ግርግዳ ላይ
በተመደበው ቦርድ ላይ
ሰቀልን፣ ፓች
ፓናሉንም ከራኩ ጋር
አያያዝነው ከኮርኒሱ
የመጡ ኬብሎችን ፓች
ፓናሉን ላይ
አገናኘናቸው(ወይም
terminated)።
- በየክፍሉ የዴታና
የፎን ኬብሎችን
በአዲሱ ማገናኛ (faceplate)
ላይ አገናኘን።
- ኔትወርኩ ክፍልም
በመመለስ ከአምስቱም
ክፍሎች የሚመጡትን
መስመሮች በፓች ፓናሉ
ላይ ካገኘን በኋላ ከ24
ፖርት ዴታ ስዊች (Data switch)
ጋር በባለሰባት ፊት
ኬብል
እናገናኛቸዋለን።
- በየክፍሉም
እየሄድን ከግርግዳው
የኔትወርክ ማገናኛ
(faceplate) ጋር
ለኮምፒዩተሮቹ
የተመደቡትን ባለ 12
ፊት ኬብሎች አንድ ጫፍ
በመሰካት፣ ሌላውን
ጫፍ ደሞ በኔትወርክ
ቴስተሩ ፖርት
በመሰካት
የኔትወርኩን
አዘረጋግ
ትክክለኝነት (signal continuity)
አረጋገጥን።
- በየክፍሉ አንዳንድ
ኮምፒዩተር
በማስቀመጥ
እያንዳንዳቸውንም
ኮምፒዩተሮች በባል 12
ፊት ኬብል አማካኝነት
ከግርግዳው ላይ
በሰራነው የዴታ
ማገናኛ (faceplate) ጋር
አገናኘናቸው።
ኮምፒዩተሮቹ በሙሉ Windows
XP-Professional ናቸው። ለምን XP-Home
Edition አልሆነም የሚል
ጥያቄ ሊነሳ ይችል
ይሆናል። ምክንያቱም
ለቢሮ ኔትወርኪንግ
ታስቦ ሳይሆን ለቤት
ጥቅም ተብሎ ስለተሰራ
ነው። በተለይ ዶሜይን
ግንኙነት ችሎታ
የለውም፣ ይህም ደሞ
የቅዳችን መሰረት
ነው።
|
|
|
|
ከዚህ
በኋላ የምናደርገው
ሰርቨሩን መገንባት፣
ከኔትወርኩ ጋር
ማገናኘት፣
ለያንዳንዳቸው
ሰራተኞች አቶ
አደፍርስን ጨምሮ
አካውንት መፍጠርና፣
ዶሜይን አካውንት
ለአካውንቲንግ፣
ለማርኬቲንግና
ፋይናንስ ማዘጋጀት፣
አቶ አደፍርስ በሁሉም
አካውንት ውስጥ
አክሰስ እንዲኖራቸው
ማዘጋጀት፣
ማይክሮሶፍት
ኦፊስንና አድቫንስድ
ኤክስኤል ዩቲሊቲስ
እያንዳንዳቸው
ኮምፒዩተሮች ውስጥ
ማስቀመጥ ይሆናሉ።
ኢሜይልን
በሚመለከት፣
ማይክሮሶፍት ኦፊስን
ኮምፒዩተሩ ላይ
ስናሰፍር
ማይክሮሶፍት
አውትሉክ አብሮ
ስለሚመጣ ይህን
በሚመለከት
የሚያስፈልገን ሴታፕ
ብቻ ማድረግ ይሆናል።
ከዚህም ጋር
እያንዳንዳቸው
ኮምፒዩተሮች ሰርቨሩ
ላይ ሎግ በማድረግ
ትክክል መስራታቸውን
አረጋግጣለሁ።
ኢንተርኔቱን
በሚመለከት፣ አሁን
ለጊዜው የኢንተርኔት
ሰርቪሱን ሴታፕ
አልጀመርንም ብሎም
በርካታ አማራጮች
ስላሉ በነሱ ላይ
የወደፊቱን ሂደት
በሚደግፍ ሁኔታ
ወደመጨረሻው ላይ
የምወስደው ውሳኔ
ይሆናል።
ይህንን
ሁሉ የነገ ስራዬ
አደረግሁት። ዛሬ
የሰራሁት አድካሚ
ነበር ምክንያቱም
ብቻዬን ቦርዱን
ግርግዳው ላይ
አስቀመጥሁ፣ አልፎም
ራኩን በቦርዱ ላይ
አደረግህ። እነዚህ
ሁለት እቃዎች ክብደት
ነበራቸው። በተለይም
ቦርዱ ሰፊ ስለሆነ
ባንድ በኩል የሚይዝ
ረዳት ያስፈልጋል፣
ለዚህም ረዳት መቅጠር
እችል ነበር። ከሴፍቲ
አንጻር ጥሩ አደራረግ
አልነበረም፣ ኮርኒሱ
ውስጥ ስገባ መሰላል
የሚይዝና አጠቃላይ
እንዲህ አይነት
ተግባር ስናከናውን
ረዳት ማዘጋጀት በጣም
ጠቃሚ ነው።
ተግባራዊ
የሰርቨር ግንባታ
በነጋታው
ጠዋት ተነስቼ ወደቢሮ
አመራሁ።
እንደደረስኩም
ክፍሎቹን ተራ በተራ
ከቃኘሁ በኋላ ቀጥታ
ወደሰርቨር ግንባታዬ
ገባሁ። ሁሉንም
ቁሳቁሶች አገናኘሁ።
በሙሉ የተገዙት
እቃዎች ሰርቨር ክላስ
ናቸው። ሰርቨሩ
24-ሰአት ስለሚሰራ
ትልቅ ሃይል ያለው ፋን
(fun) ገዝቼያለሁ።
እንደሌሎቹ ቁሳቁሶች
ሁሉ እሱም ቦታ አለው።
የኮምፒዩተሩ ዋናው
አካል (ወይም case) ሰርቨር
ክላስ ስለሆነ በቂ
የአየር መዘዋወሪያ
አለው። ውስጡን
በደንብ ካየሁ በኋላ
በኬዙ ታችኛው አካል
ላይ ዋናውን ቦርድ (motherboard)
አስቀመጥነው።
የገዛነው ኬዝ ራክ
ማውንት ነው። ሁለት
ሀርድ ድራይቮሽ
አሉን፣ አንዱ ውስጥ
ሲሆን ሁለተኛው ደሞ
ውጭ የሚሆኑ ናቸው።
የውስጠኛው
የሲስተማችን ሲሆን፣
የውጭውን ደሞ ለባካፕ
እንጠቀምበታለን።
ሁለቱን ሃርድ ድራይቭ
እንደሁኔታቸው
ገጥመን አስቀመጥን፣
ከዚያም ሲዲ ራሙን
ገጠምን፣ የገዛነውን
4GB ራም ሜሞሪ በቦታቸው
ሰካናቸው። እነዚህን
ዝቅተኛ ቮልቴጅ
ኤሌክትሮኒስክ
እቃዎች በጃችን
ስንይዝ ከስታቲክ (Static)
ጥንቃቄ ማድረግ
ያስፈልጋል፣ ለዚህ
አይነት ሰራ ሶሉ
ላስቲክ ያለው ጫማ
ማድረግ አለዚያም
ግራውንድ (anti-static) በጃችን
ላይ ማድረግ
ያስፈልጋል። ችፕሶቹ
በጣም ጥንቃቄን
ይፈልጋሉ። ሁሉን
ከሰካካን በኋላ
በመጨረሻ ኬዙን
ገጠምን።
በተመደበለት
የማያቋርጥ የሃይል
ምንጭ (Uninterrupted Power Supply – UPS) ላይም
ሰካነው። የዚህ UPS እቃ
አገልግሎቱ
ኤሌክትሪክ
ሲያቋርጥ፣ ወዲያውኑ
ቦታውን በመያዝና
ለሰርቨሩ የማያቋርጥ
ሃይል ምንጭ ቢያንስ
ለሁለት ሰአት መስጠት
ይሆናል። ሰርቨሩ
በድንገት ኤሌክትሪክ
ሲቋረጥና በቅጽበት
ሲጠፋ፣ እንደገና
ስናስነሳው ብዙ
ችግሮች ሊገጥሙን
ስለሚችሉ የዚህ UPS
አገልግሎች አይነተኛ
ነው።
እዚህ
ላይ ሰርቨር ማጣመሩ
አለቀ፣ አሁን
የመጀመሪያውን
የባዮስ (ወይም
የሲስተም
ዲያግኖይስቲክ) ሂደት
መኖሩን ማረጋግጥ
አለብኝ።
የኮምፒዩተሩንም
ሃይል ምንጭ ከተጫንኩ
በኋላ ወደሞኒተሩ
በመመልከት የሲስተም
ባዮሱን
ኢንፎርሜይሽኖች
አስተካከልኩ።
በተለይም Plug and Play ሲስተሙ
በተለምዶ ON ሲሆን
ወደተቃራኒው መቀየር
አለብን፣ OFF
አደረግሁት። የቀረው
ነገር ምንም
አይቀየርም፣ ማድረግ
ያለብን ሃርድ
ድራይቮቹና ሲዲ ሮሙ
መታወቃቸውን
ማረጋገጥ ነው። ይህን
ሁሉ ካደረግን በኋላ
የሊኒክስ ሲዲያችንን
በማውጣት
የመጀመሪያውን ሲዲ
በሲዲሮሙ ውስጥ
ከተትኩት።
ኮምፒዩተሩን
እንደገና ስንጀምር
ሌላ ቡተብል እቃ
(ወይም ዲቫይስ)
ስለሌለ በቀጥታ
ወደሲዲው ሲሄድ
የመጀመሪያው ሴክተር
ቡት የሚያደርግ
ፋይሎችን ስለያዘ
ወዲያው የሊኒክስን
ኢንስታሌሽን ሂደት
ይጀምራል።
በነገራችን ላይ
የምጠቀመው የሊኒክስ
ሲስተም
እንደጠቀስኩት
የሬድሃት ፌዶራ ኮር 6
ነው።
ኢንስቶሌሽን
ከመቀጠሌ በፊት ሁሉን
ነገር በደንብ መጻፌን
አረጋገጥኩ፣ ማለትም
ስለሲስተሙ አጠቃላይ
ኢንፎርሜይሽኖች
አሉኝ።
አብዛኛውን
ጊዜ ሊኒክስ
ቁሳቁሶችን ሁሉ
ማወቁን ይነግራል።
በተለይ አንድ ትልቅ
ችግር ሞኒተር ላይ
ሲሆን Monitor probing የሚል
ይመጣና በቂ
ኢንፎርሜይሽኖችን
ካላገኘ ለጋራ
አገልግሎት የሚውል
(ወይም generic setup) ለማድረግ
ይሞክራል። ይህም
የማይሰራበት ሁኔታ
ሊፈጠር ይችላል።
ስለዚህ ሁሉን
ኢንፎርሜይሽን
አዘጋጅቶ ማስቀመጡ
ይጠቅማል።
ማወቅ
ያሉብን ነገሮች፡
- ፌዶራ ኮር ቨርዥን 6
በትንሹ ለከርናሉ ብቻ
የሚጠይቀው 700MB ድራይቭ
ቦታ ነው። ነገር ግን
አፕልኬሽኖችን
ለማስቀመጥ ቢያንስ 3
GB በቀላሉ
ይፈልጋል።
- በቅድሚያ መሰራት
ያለባቸውን ነግሮች
በሙሉ እንደቅደም
ተከተላቸው መሰራት
ይገባቸዋል።
በተለምዶ ፌዶራ
ሊኒክስ የዲ.ኤች.ሲ.ፒ
ሰርቨርን ለመፈለግ
ይሞክራል
ትክክለኛውን
ኔትወርክ ግንኙነት
ለማወቅ። በዚህ
አጋጣሚ ሊኒክስ
ሰርቨር ለቢሮ
አገልግሎት ብቻ
ስለሆነ፣ ከውጭ
በጭራሽ እንዲታይ
አንፈልግም፣
ስለዚህም ምንም
እንኳን በተሰጠው
የኢንተርኔት
ግንኙነት ላይ አንድ
ኮምፒዩተር ብቻ
እንዲመልስ
ብናዘጋጅም የሳንባ
ሰርቨር ትራፊክ
ለሎካል ኔትወርክ
ብቻ።
- ኮምፒዩተሮቹ ምንም
እንኳን የኢንተርኔት
ተጠቃሚዎች ቢሆኑም
በሙሉ ከውጭ አይታዩም
(will use masquerading)። ነገር ግን
በኮምፒዩተሮቹ ስም
ሆኖ የውጭውን
ግንኙነት በትጋት
የሚሰራ ኮምፒዩተር
ይኖረናል።
- የፌዶራን
ኮር 6 ሲስተም ሙሉ
ለሙሉ በኮምፒዩተሩ
ለማስቀመጥ 5 ዲስኮች
አሉኝ። ነገር ግን
ሁሉንም ሲስተሞች
በዚህ አጋጣሚ
አልፈልጋቸው፣
ምናልባት ከ3 ሲዲ
በላይ አይፈልግም ብዬ
እገምታለሁ ሰርቨሩን
ለመገንባት።
ምክንያቱም ሳንባን
ብቻ ነው የምገነባው።
|
|
|
|
|
|
የሊኒክስ
ሰርቨር ሶፍትዌር
ግንባታ
|
የፌዶራ
ሊኒክስን ሲስተም
ለማስቀመጥ
የመጀመሪያውን
ቡተብል ሲዲ ሲዲሮም
ውስጥ በመክተት
ኮምፒዩተሩን
እንደገና አስነሳሁት
(ወይም rebooted) ። ከዚህ
በኋላ ደረጃ በደረጃ
በአዲሱ ኮምፒዩተር
ላይ የሚጠየቀውን ሁሉ
በማሟላት በሚከተለው
መልክ ሰርቨሩን
ገነባሁት።
- በመጀመሪያ
የቡት ስክሪን ይመጣል
ከታች እንድሚታየው።
ሌላ ቡት ዲቫይስ
ስለማልፈልግና ቀጥታ
አሁን ቡት
ያደረገበትን
ዲባይስ፣ ማለትም
ሲዲውን፣ ስለሆነ
የምጠቀመው ኢንተር (Enter)
የሚለውን ኪቦርዱ ላይ
ተጫንኩ። ከታች
እንድምናየው
የግራፊካል
ኢንስታሌሽን ጭምር
ነው ከምርጫችን ጋር
የሚከተለው።

- ቀጥሎም
ሲዲ መፈተን ሲሆን
የሚቀጥለውን
እናያለን። OK የሚለው
ተመርጧ ኢንተር (Enter)
የሚለውን ተጫንኩት።

- ከላይ
ቴስት ያደረገበትን
ውጤት ያቀርባል።
በዚህ አጋጣሚ ውጤቱ
ጥሩነው ከታች
እንደሚታየው።
ለመቀጠልም OK
የሚለውን ተጫንኩ።
|
|
|
|
|
|
- ቀጥሎም
ተጨማሪ ሲዲ ቴስት
ማድረግ ትፈልጋለህ
ወይ የሚል ሲሆን
አምስቱንም ማድረግ
ስለምፈልግ
ሁለተኛውን ሲዲ
በመክተት Test የሚለውን
ተጫንኩ። ሁሉንም
እንደጨረስኩ
የመጀመሪያውን ዲስክ
እንደገና እንከታለን
ከዚያም Continue የሚለውን
ከመረጥሁ በኋላ
ከኪቦርዱ ላይ Enter
የሚለውን ተጫንኩ።

- ቀጥሎም
በሲስተሙ ውስጥ
የምንጠቀመውን ቋንቋ
ይጠይቃል።
እንግሊዝኛ ዲፎልቱ
ነው እሱን እንዳለ
በመቀበል Enter አደረግሁ
ከኪቦርዱ።

- የሚቀጥለው
የኪቦርድ መስተካከል
(Configuration) ሲሆን ያለውን
በመቀበል ከኪቦርዱ
ታብን (Tab) በመጫን OK
የሚለውን ከመረጥሁ
በኋላ Enter የሚለውን
ተጫንኩት።
- ቀጥሎም
ኮምፒዩተሩ ላይ
የምናሰፍረውን
ፕሮግራሞች የያዘውን
አካል (ወይም source)
ይጠይቀናል፣
ከሲዲሮም ስለሆነና
እሱን ስለተመረጠ፣
ከኪቦርዱ ላይ ታብን (Tab)
ከተጫንን በኋላ OK
የሚለውን እንመርጥና
ከኪቦርዱ Enter የሚለውን
ተጫንኩት።

|
|
|
|
|
- ከዚህ
በመቀጠል ዌልካም
የሚለው ይመጣል፣
በቀጥታ Next የሚለውን
በማውሱ (mouse) ክሊክ
አደርግሁት።

|
- የሚቀጥለውም
የምንገነባው ሲስተም
አዲስ ወይስ ባለው ላይ
(upgrade) ነው የሚል ምርጫ
ሲሆን የምሰራው አዲስ
ኢንስቶሌሽን ስለሆነ
Install Fedora Core የሚለውን
ከመረጥሁ በኋላ Next
የሚለውን በማውሱ
ክሊን አደረግሁ።

- የሚቀጥለው
ሂደት ፓርቴሽን ሲሆን
በተለምዶ (default)
የተመረጠውን
ከተቀበልኩ 3 ፓርቴሽን
ያደርጋ። ይህም፡ 1. /boot 2. /
3. Swap ፓርቴሽን ናቸው።
ነገርግን ከዚህ በላይ
ፓርቴሽን መጨመር
እንችላለሁ ወይም
የተለመደ አሰራር
ነው። ለምሳሌም ብዙ
የተጠቃሚዎችን ዴታ (data)
ሰርቨሩ ማናጅ
የሚያደርግ ከሆነ /home ፓርቴሽን
መጨመር ጠቃሚ ነው።
የምንፈልገውን
ፓርቴሽን
አስተካክለን
ከጨረስን በኋላ Next
የሚለውን
እንጫናለን።

- በሊኒክስ
እና ዩኒክስ አጠቃቀም
ውስጥ የምናያቸው
ፓርቴሽኖች አይነት -(/usr፣
/usr/local፣ /var፣ /boot፣ /home…)
የሚያሳዩት የዚያን
ፋይል ሲስተም ፎርማት
ይሆናል። ስለዚህም
የሚቀጥለው ስእል
የሚያሳየው እነዚህን
ፓርቴሽኖች እንዴት
እንደምናዘጋጅ
ይሆናል። ለዚህም
አጠቃቀም Disk Druid የሚባል
የፓርቴሽን
ቴብላችንን
በምንፈልገው መልክ
ሊሰራ የሚችል
ፕሮግራም ሲሆን
ከዚሁም ጋር አብሮ
ዲስክ RAID እና LVM(Logical Volume Mgmt)
ኮንፊገር ማድረግ
ያስችለናል።
የምንገነባው ሲስተም
አዲስ ስለሆነ፣ New
የሚለውን በመጫን
የምንፈልጋቸውን
ፓርቴሽኖች ተራ በተራ
እንጨምራለን።
ከዚያም Next የሚለውን
በመጫን
እንቀጥላለን።

|
|
|
|
|
|
- ከታች
የምናየው boot loader የሚባል
አነስተኛ ፕሮግራም
ሲሆን ከአንድ በላይ
ኦፕሬቲንግ ሲስተም
በኮምፒዩተራችን ላይ
ማስፈር ከፈለግን
ማዘጋጀት ይረዳናል።
ሲስተሙን
በምንጀምርበት ጊዜ
የትኛውን ኦፕሬቲንግ
ሲስተም መጠቀም
እንደምንፈልግ ምርጫ
ይሰጠናል። ይህ
ሊኒክስ ሰርቨር
ብቻውን ስለሆነ
በቀጥታ Next የሚለውን
በማውሱ በመጫን
እቀጥላለሁ።

- ነገር
ግን ተጨማሪ ቡት
የሚያደርግ
ኦፕሬቲንግ ሲስተም
ካለና በሜኒዩ (Menu) ውስጥ
እንድናስቀምጠው
ከተፈለገ Add የሚለውን
በማውሱ ስንጫን
የሚከተለውን
እናያለን፣ ከዚያም
እንዲጨመር
የምንፈልገውን
ኦፕሬቲንግ ሲስተም
በተሰጠው ሳጥን ውስጥ
እንሞላለና OK
የሚለውን በማውሱ
ከተጫንን በኋላ Next
የሚለውን በማውሱ
በመጫን
እንቀጥላለን።

- ሌላ
ሰው ሰርቨሩን አክሰስ
የሚያደርግበት
ምክንያት ስለሌለ፣
ከአቶ አደፍርስ
በቀር፣ የ GRUB ፓስወርድ
መፍጠር
አያስፈልግም።
ስለዚህም Next የሚለውን
በመጫን እቀጥላለሁ።
- የሚቀጥለው
የፌዶራ ሊኒክስ
አድቫንስድ ቡት
ምርጫዎች ሲሆኑ፣
በተለምዶ የተመረጠው
በቂ ስለሆነ፣ ከታች
እንደሚታየው፣
እንዳለ ሆኖ በማውሱ Next
የሚለውን በመጫን
እቀጥላለሁ።

- ቀጥሎም
ኔትወርክ
ኮንፊዩግሬሽን
ሲሆን፣ የሚቀጥለው
ፎቶ የሚያሳየን ቋሚ
አይ.ፒ (static IP) አድራሻ ነው
ወይስ ቋሚ ያልሆነ
አይ.ፕ አድራሻ (DHCP)
ምርጫችን የሚለውን
እንድንመልስ ነው።
ይህንን ለመወሰን
ምንድነው መሰረታችን?
-
- በመጀመሪያ
ሰርቨራችን
ከኢንተርኔት
እንዲገናኝ
ፍላጎታችን
አይደለም። ነገር ግን
አምስቱ ኮምፒዩተሮች
ኢንተርኔት መገናኘት
አለባቸው።
- ለሁሉም
ኮምፒዩተሮች የውጭ
ግንኙነት የሚሰጠው
ሞደሙ ነው።
- በዚህ
ሁኔታ መሰረት
በማድረግ ከውጪ
ወደሰርቨራችን
የሚመጣን ትራፊክ
ማገድ መቻል አለብን።
- የኢንተርኔት
ትራፊክ የሚፈሰው ወደ
ዴስክቶፕ
ኮምፒዩተሮቹ ብቻ
ነው።
- ይህንን
ሁኔታ መሰረት
በማድረግ የአይ.ፒ
አድራሻ እቅድ
እናወጣለን።
ሰርቨራችንና
ፕሪንተራችን ቋሚ
የሆነ አይ.ፒ አድራሻ
እንመድብላቸዋለን፣
ይህም አይፒ አድራሻ
ኢንተርኔት ላይ
ራውተብል ወይም
ተጠቃሚ ሊሆን
የማይችል - ወይም
ፕራይቬት አይ.ፒ
አድራሻ ነው።
የኢንተርኔት ቁጥርን
የሚመድብ ክፍል Internet Assigned
Numbers Authority (IANA) የሚከተሉትን
ለዚሁ ፕሪቬት አይፒ
አድራሻ እንዲሆኑ
መደቧል።
- 10.0.0.0 - 10.255.255.255
- 172.16.0.0 - 172.31.255.255
- 192.168.0.0 - 192.168.255.255 (ያሉን
ኮምፒዩተሮች ትንሽ
ስለሆኑ ይህንን
እጠቀማለሁ)
- 169.254.0.0 -169.254.255.255 (ይህን
አይ.ፒ አድራሻ
ልንጠቀምበት
አንችልም፣
አውቶማቲካሊ
ከኮምፒዩተራችን
ውስጥ የሚያቸው
ቁጥሮች ናቸው። ይህ
ሲሆን ኮምፒዩተራችን
ከውጪ ጋር ግንኙነት
ሊያደርግ አልቻለም)
- ከመጀመሪያዎች
ሶስቱ የትኛው ለኛ
ይጠቅመናል የሚለውን
ለመመለስና በጥቅም
ለማዋል፣ 192 የሚለውን
እንወስዳለን።
ምክንያቱም ከአንድ
በላይ ኔትወርክ
አይኖረንም አቶ
አደፍርስ የአንዱን
ኜትወርክ ወሰን
የሚሞሉ ከምፒዩተሮች
ለመጨመር ምናልባት
በርካታ አመታቶች
ሊወስድ እንደሚችል
እገምታለሁና በዚህ
ምክንያት የዚህ አንድ
ኔትወርክ እስከ 254
ከምፒዩተሮች፣
የኔትወርክ
ፕሪንተሮችና
የኔትወርክ
ዲቫይሶችን ሊይዝ
ይችላል።
- ከላይ
በተጠቀሱት መሰረት
የሚከተለውን ሴታፕ
እናደርጋለን። Network Devices
በሚለው ሳጥን ውስጥ
ያለውን ከታች
እንደምናየው በማውሱ
በመጠቆም ክሊክ
አድርገን ትኩረት
ከሰጠነው በኋላ፣
እንደሚታየው ክሊክ
ያደረግንበት
ጠቁሮዋል፣ ከዚያም Edit
የሚለውን ክሊክ
ካደረግን በኋላ የሆነ
ስጥን ይታያል። ከዚህ
በኋላ ሲስተሙ
በተለምዶ የሚለውን
መርጦታል፣ ይህንን
ቼክ ማርክ
እናስወግዳለን
ምክንያቱም
የምናደርገው ሴታፕ
ስታቲክ አይ.ፒ (ወይም
static IP) እንጂ ዳይናሚክ (DHCP)
አይደለምና።
ቀጥለንም አይ.ፒ
አድራሻ ለሰርቨራችን
እንመድባለን፣ ይህም
192.168.0.2 ይሆናል፣ ኔት
ማስክ (ወይም network mask) ደሞ
፡ 255.255.255.0 ይሆናል።
ጌትዌይ (ወይም gateway)
ደሞ፡ 192.168.0.1 ።
|
|
|
|
|
- ከጥሎም
የሰርቨር ስም (Hostname)
ከታች ያለው ስእል
ይጠይቃል። Manually
የሚለውን ከመረጥን
በኋላ የሰርቨሩን ስም
እናስቀምጣለን።
የጠሟላ ሰም machine.domain.com
ሲሆን። ስም ስናወጣ
በዘፈቀደ ማድረጉ ጥሩ
ምርጫ አይደለም።
ትክክለኛ ሴታፕ
ማድረግ አስፈላጊ
ነው። ስለዚህም እኔ
ስም ሳወጣ
የወሰድኩት፦
ያለንበት ከተማ አዲስ
አባባ (aa)፣ አካባቢው
ከአራት ፊደል
ባልበለጠ(bole)፣ የዚህ
ሰርቨር ስም - ሳምባ (smb)፣
የመጀመሪያ ሰርቨር
(01)። የዚህ ሰርቨር
ስም፡ aabolesmb01 ይሆናል
ይህንንም ከታች ባለው
ቦክስ አሰፈርን።

|
- ቀጥሎም
የሲስተሙን ሰአት (time zone)
እናስተካክላለን
ከታች እንደሚታየው.
ይህንንም ለማድረግ
ሁልት ምርጫዎች
አሉን። አንደኝው
ኢትዮጵያ ላይ ማውሱን
በመጠቆም አቅራቢያ
የሆነውን ነጥብ
በማጉላት እያሳየን
ሱንም በመግለጽ
ያለበትን የጊዜ ክልል
ይሳየናል፣ ማውሱን
ክሊክ በማድረግ
ትክክል መሆኑን
እናረጋግጣለን።
ሁለትኛው፣ ከአለም
ካርታ በታች በስተግራ
በኩል ያለውን አራት
ማእዘን ተከፋት (dropdown menu)
በማውሱክሊክ
በማድረግ
የኢትዮጵያን የጊዜ
ክልል መምረጥ ነው።
ከዚያም በማውሱ Next
የሚለውን በመጫን
እንቀጥላለን።

- ቀጥሎም
የአድምንስትሬተር
(ወይም root) ፓስወርድ
እንድንፈጥር
ይጠይቀናል።
አድምንስትሬተር (root)
አካውንት በሊኒክስ
ሲስተም ውስጥ እንደ
ተጠቃሚው (user) ገደብ
የለበትም፣ ስለዚህም
የሲስተሙ ባለቤት
በመባል ይታወቃል።
ቀጥለንም የዚህን
አካውንት ፓስወርድ
ከፈጠርን በኋላ
በማውሱ Next የሚለውን
በመጫን
እንቀጥላለን።

- ቀጥሎም
በግንባታችን ውስጥ
የምንጨምራቸውን
ሶፍትዌሮች
ያሳየናል። ለኛ
ግንባታ ጥቅም ያለው
software development የሚለው ብቻ
ስለሆን እሱን
እንመርጥና ሌሎቹን
ተመርጠው ከሆን ቸክ
ምርኩን
እናስውግዳለን፣
ከዚያም Next የሚለውን
በመጫን
እንቀጥላለን። Add additional software
repositories አንፈልገውም።

|
|
- Add additional software repositories የሚለውን
የምንጠቀመው
ኢንተርኔት ግንኙነት
ካለን ነው። ይህንን
አንፈልገውም
በማውሱም መጫን
አያስፈልግም።

|
|
|
- ቀጥሎም
ሶፍቴር
የምንመርጥበት ሂደት
ሲሆን የምንፈልገውን
እንድንመርጥ እድል
ይሰጠናል።
በመጀመሪያ በግራ
በኩል ካሉት ክሊክ
በማድረግ በቀኝ በኩል
ከሚሰጠን ሊስቶች ፊት
ለፊታቸው ካለው ሳጥን
ውስጥ በማውሱ ክሊክ
በማድረግ መምረጥ
ያስፈልጋል
የያዛቸውን ነጠላ
ሶፍትዌሮች
ለመምረጥ፣ ከዚያም22 ን
እናያለን።

- በዚህ ቡድን
ውስጥ ያሉትን
ሶፍትዌዎርች በሙሉ
ያሳየናል ከታች
እንደምናየው።
የምንፈልጋቸውን
ከፊትለፊታቸው ባለው
ቦክስ ክሊክ በማድረግ
ከመረጥን በኋላ Close
የሚለውን በመጫን
ከዘጋነው በኋላ Next
የሚለውን መጫን
እንቀጥላለን።
- የሚከተሉ
ከማንኛውም ፌዶራ
ሊኒክስ ግንባታ ጋር
አብረው በተለምዶ
ይኖራሉ፡
- ሴንትራላይዝድ
የሆን ሎግ በ syslog
አማካኝነት
ይካሄዳል።
- ኢሜይል ደሞ በ SMTP (Simple Mail
transfer Protocol) አማካኝነት
ይካሄዳል።
- የኔትወርክ ፋይል
መጋራት በ NFS (Network File System)
አማካኝነት
ይካሄዳል።
- ከሌላ ኔትወርክ ሆኖ
ሲስተም ውስጥ መግባት
(ወይም remote login) የሚቻለው በ
SSH (Secure SHell) አማካኝነት
ነው።
- ቁሳቁስ ትውውቅ (advertising)
የሚካሄደው በ mDNS (multicast DNS)
አማካኝነት ነው።
- ፋይል ትራንስፈር (file
transfer) የሚካሄደው በ HTTP (HyperText
Transfer Protocol) አማካኝነት
ነው።
- ፕሪንቲንግ (Printing)
የሚካሄደው በ CUPS (Common UNIX Printing
System) አማካኝነት ነው።
- ከሌላ
ቦታ ሆኖ
ኮምፒዩተራችንን
አክሰስ ለማድረግ (remote desktop access) በ
VNC (Virtual Network Computing) አማካኝነት
ይካሄዳል።

- ሳንባን
ከሰርቨር ውስጥ
ከመረጥን በኋላ፣
ከግሩፑ ደሞ ሁሉንም
እንመርጣለን
ምክንያቱም በሙሉ
የምንፈልጋቸው
ናቸው።
- ቀጥሎ
የሚታየው ምን ነገር
የሚመረጥ የለውም
በማውሱ Next የሚለውን
በመጫን
እንቀጥላለን።

- ቀጥሎም
የመረጥናቸውን
ሶፍትዌሮች መገንባት
ይጀምራል፣ ይህም ጊዜ
ይፈጃል። ከታች
የሚታየው
የሶፍትዌሮቹ ግንባታ
እድገታቸውን ነው።
ይህ ሂደት ሲያልቅ Reboot
የሚል ይመጣል እሱን
በማውሱ በመጫን
ኮምፒዩተሩ
አውቶማቲካሊ ከጠፋ
በኋላ ይጀምራ።

|
|
|
|
|
|
ከላይ
የምናየው ሶስት
መስመር የሚሰራው፣
የመጀመሪያው
የሳንባን ፓስወርድ
ፋይል በ /etc/samba
ዳይሬክተሪ ውስጥ
ከፈጠረ በኋላ ከዋናው
ፓስወርድ ወደሱ ኮፒ
ያደርጋል።
ሁለተኛው
መስመር ደሞ
ለተፈጠረው ፓስወርድ
የአድምንስትሬተር
(ወይም በሊኒክስ
አጠራር root)
ባለቤትነትን
ይፈጥራል።
ሶስተኛው
መስመር የሳንባን
ተጠቃሚ ፓስወርድ
ይፈጥራል።
እንደተነጋገርነው
በዋናው የሲስተም
ፓስወርድ ውስጥ አራት
አካውንቶችን
ፈጥረናል፣ ከአቶ
አደፍርስ ጭምር።
ስለዚህም ለነዚህ
አካውንቶች በሙሉ
የሳንባ ፓስወርድ
እንፈጥራለን።
ሳንባ
ለሎካል ኔትወርክ
የከፈተውን በር (ወይም
Ports- ለምሳሌም 137፣ 138፣ 139፣
445፣ 901) ለኢንተርኔት
ትራፊክ ክፍት
እንዳይሆኑ ማገድ
አለብን ወይም ሳንባ
ምንም አይነት ሰርቪስ
ለኢንተርኔት
ማቅረብና ማጋለጥ
የለበትም። ለዚህም
ፋየርወል ማዘጋጀት
አለብን። ኢንተርኔት
ግንኙነት ስንፈጥር
የሚፈቀዱ ፖርቶች (ports)
80(HTTP)፣ 443(HTTPS) ፣ 25(Email)፣ 53(DNS) ብቻ
መሆን አለባቸው፣
ቢያንስ ላሁኑ።
ወደፊት አስፈላጊነት
ሲኖር የምንከፍታቸው
ፖርቶች ይኖራሉ።
በ PAM (Plugable Authentication Module) አማካኝነት
/etc/pam.d/samba ፋይል መኖሩን
እናረጋግጣለን።
ሳንባን ስንገነባ /etc/pam.d
ዳይሬክተሪ ውስጥ
ከሚቀመጡት አስፈላጊ
ፋይሎች ውስጥ አንዱ
ፓም (PAM) ተመንክሮ ያለው
የሳንባ ፋይል ነው።
ሴታፕ የምናደርገው ሰርቨር
ዶሜይን ላይ
የተመሰረተ (PDC=Primary Domain Controller)
ሲሆን፣ የዎርክግሩፕ
(Workgroup) ስሙም aabolesmb01
ይሆናል። ይህንን ሁሉ
ከታች ባለው የ smb.conf
ፋይል ውስጥ
እናያለን።
ቀጥለንም
አድምንስትሬተር
አካውንት (admin account) መፍጠር
አለብን። እዚህ ላይ
መጠንቀቅ ያለብን፣
ከሊኒክስ
አድምንስትሬተር
አካውንት ጋር መማታት
የለበትም። በተቻለ
መጠንም ከሲስተሙ ሩት
ፓስወርድ መለየት
አለብን።
[root@aabole01 home]# smbpasswd –a root
|
አሁን
ለምንተክለው
ክላይንት/ሰርቨር
ግንኙነት ተጠቃሚ (user)
ላይ የተመሰረት
ሎግኢን ግልጋሎት ላይ
እናተኩራለን፣ ከዚህ
ጋር ሮሚንግ ፕሮፋይል
(roaming profile - አገልግሎቱ
በምንጠቀምበት
ኮምፒዩተር ሁሉ
የኔትወርክ
አካውንታችን አብሮ
እንዲሄድ ይረዳል)
ቀጥለንም
የሳምባ ተጠቃሚ
ፋይልን
እንፈጥራለን።
ይህንን ለማደርግ
መጀመሪያ በ /etc/samba
ዳይሬክተሪ
እንሆናለን
ኮማንድላየን (commandline)
በመሄድ የሚከተለውን
እናደርጋለን፦
[root@aabole01 home]# cd /etc/samba
ከዚያም
የሳምባ ተጠቃሚዎች
ፋይል መኖሩን
እናጣራለን ወይም
እንፈጥራለ፣ ከዚሁም
ጋር አድምንስትሬተር
የዊንዶውስና
የሊንክስ
አድምንስትሬተር
አካውንት መኖሩን
እናጣራለን ወይም
እዚያው
እንጨምራለን። ይንን
ለማድረግ
ከኮማንድላየን ላይ
ሆነን የሚከተለውን
እናደርጋለን፡
root@aabole01 home]# vi smbusers
የ
vi ኢድተር ሲመጣ፣ vi
ን ፊደል ከኪቦርዱ
አንዴ በመጫን
የሚከተለውን ታይፕ
እናደርጋለን፣ ካለም
ሴቭ አድርገን ፋይሉን
እንዘጋለን።
root=administrator
ከዚያም
<ESC> የሚለውን
ከኪቦርዱ ላይ
ከተጫንን በኋላ
የሚከተለውን
ከኪቦርዱ ላይ ታይፕ
እንድርጋለን
:/wq!
|
|
ይህ
ፋይል የሳንባ
ተጠቃሚዎች፣
በተለይም ሩት
አካውንት ከዊንዶውስ
አድምንስትሬተር
አካውንት ጋር
ለማመሳሰል ይረዳል።
ቀጥለንም
የሳንባን
ኮንፊግሬሽን ፋይል
በመክፈት
የተነጋገርናቸውን
በሙሉ
እናስቀምጣለን።
ይህንን ለማድረግ
በመጀመሪያ ሳንባ
ዳይሬክተሪ
እንሄዳለን
ከተርምናል ሳጥን
ውስጥ ሆነን
የሚከተለውን ታይፕ
እናደርጋለን፡
[root@aabole01 home]# vi smb.conf
ፋይሉ
ስላለ በወቅቱ መጠነኛ
የኮንፊዩግሬሽን
መግቢያዎች ይኖሩት
ይሆናል ነገር ግን
በሚከተለው መልክ
ይህንን ፋይል
አስተካከልኩት።
[global]
# በግሎባል
ስር የሚቀመጡት
አጠቃላይ ህጎች ናቸው
netbios name = samba
#
ዶሜይን ሰርቨራችን
ከታች እንደሚታየው
ነው። በዊንዶውስ
ውስጥ የኔትወርክ
ድራይቭ
#
ለመስራት ከፈለግን
ይንን ወርክግሩፕ ስም
ነው የምንጠቀመው
workgroup = aabolesmb01
server string = samba server
interfaces = eth0 , lo
encrypt passwords = yes
#
ወደፊት የሰራተኛ
ቁጥር እየጨመረ
ከመጣና ብዙ
አፕልኬሽኖች ውስጥ
ለመግባት ዩዘር ስምና
#
ፓስወርድ የሚፈለግ
ከሆነ፣ በርካታ
ሳብኔቶች ካሉ…
መሰረታዊ መልስ አሁን
የፈጠርነውን
#
የፓስወርድ ፋይል
ዴታቤዝ ላይ መሰረት
ባለው ፓስወድ ፋይል
እንቀይረዋለን።
smb passwd file = /etc/samba/smbpasswd
unix password sync = yes
wins support = yes
#
ይህ
የሳንባ ሎግ ፋይል
ነው፣ ማነኛውም
ክንውን በዚህ ሎግ
ውስጥ ይኖራል።
log file = /var/log/samba/log.%m
max log size = 65
smb ports = 139
name resolve order = wins bcast hosts
time server = Yes
hosts allow = 192.168.0. 127
printcap name =/etc/printcap
load printers = yes
printing = cups
cups options = Raw
security = user
unix password sync = yes
passwd program = /usr/bin/passwd %u
passwd chat = NewUNIX*password* %n\n reType*new*UNIX*password* %n\n passwd:all*authentication*tokens*updated*successfully*
ከታች የሚያሳየን
የሳምባ ተጠቃሚዎች
ፋይል ነው።
username map = /etc/samba/smbusers
socket options = TCP_NODELAY SO_RCVBUF=8192 SO_SNDBUF=8192
ሳምባ የሁሉም ማስተር
ፕሮግራም ነው
Local master = yes
Domain master =yes
Preferred master = yes
os level = 65
Domain logons = yes
Logon path = \\%L\Profiles\%u
Logon script = logon.bat
Logon drive = H:
Logon home = \\%L\%u\.win_profile\%m
Add user script = /usr/sbin/useradd –d /divnull –g 100 –s /bin/false –M %u
Add user script = /usr/sbin/useradd –m ‘%u’
Delete user script = /usr/sbin/userdel –r ‘%u’
Add group script = /usr/sbin/groupadd ‘%g’
Delete group script = /usr/sbin/groupdel ‘%g’
Add user to group script = /usr/sbin/usermod –G ‘%g’ ‘%u’
Add machine script = /usr/sbin/useradd –s /bin/false –d /var/lib/nobody ‘%u’
#===========Belowis Share definition===============
[homes]
comment = Home Directories
read only = no
browseable = no
guest ok = no
map archive = yes
[netlogon]
comment = Network Logon Service
path = /home/netlogon
guest ok = yes
writable = no
share modes = no
[Profiles]
path = /home/ profiles
browseable = no
writable = yes
guest ok = yes
create mask = 0600
directory mask = 0700
[printers]
comment = SMB Print Spool
path = /var/spool/samba
guest ok = Yes
printable = Yes
use client driver = Yes
default devmode = Yes
browseable = No
#
Below is accounting group, can login only if privileged
[accounts]
comment = Accounting Files
path = /usr/accounts
read only = No
valid users = adeferes
|
|
|
#
Below is marketing group, can login only if privileged
[markets]
comment = Accounting Files
path = /usr/markets
read only = No
valid users = adeferes
[apps]
comment = Applications
path = /samba/apps
public = no
writable = no
printable = no
create mask = 0666
directory mask = 0775
# force group = samba
# force user = samba
hide dot files = yes
admin users = adeferes
[Share]
path = /home/Share
writable = yes
guest ok = yes
public = yes
force create mask 0777
force directory mask 0777
force create mode 0777
force directory mode 0777
browseable = yes
[av-updates]
comment = Antivirus updates
path = /samba/data/av-def/update
public = yes
writable = no
printable = no
guest ok = yes
hide dot files = yes
[Webaccess]
comment = Apache DocumentRoot
path = /home/httpd/html
valid users = adeferes accouts markets finance secretary
public = no
writable = yes
#
እዚህ ላይ
የኮንፊግሬሽን ፋይሉ
ያልቃል
ከዚህ
በኋላ ፋይሉን ሴቭ
እናደርግና ከፋይሉ
እንወጣለን። ከዚያም
ሳንባ ሲስተም
እንዲካሄድ ሳንባ
ሲስተም ማስላት
ያስፈልገናል።
ከኮማንድላየን
ላይ ሆነን
የሚከተለውን
እንደርጋለን።
[root@aabole01 home]# cd /etc/samba
ይህ ወደሳንባ ድይሬክተሪ
እንዲንሄድ
ያደርገናል። ከዚያም
ሳንባ ስራ እንዲጀምር
እናደርጋለን፡
[root@aabole01 home]# /etc/rc.d/init.d/smb start
ወይም
[root@aabole01 home]# service smb start
አሁን ሳንባ ተጀመረ ማለት
ነው። ቀጥለንም
ሲስተማችን ሲጀምር
ሁልጊዜ ሳንባ አብሮ
እንዲጀምር ማድረግ
አለብን።
[root@aabole01 home]# chkconfig add smb on
የሰራነውንም
የሳንባ ሰርቨር
ለመፈተን
የሚከተለውን
ኮማንድላየን ላይ
ታይፕ እናድርጋለን።
ይህ የሚያደርገው
የሳንባ ሰርቨር አሁን
ለመስጠት
ያዘጋጃቸውን
ሰርቪሶች በሙሉ
ያሳየናል።
[root@aabole01 home]# smbclient -U% -L localhost
ቀጥለንም
የአራቱን ሰዎች
አካውንት
እንፈጥራለን።
እያንዳንዳቸው
ኮምፒዩተሮች ሁለት
አይነት አካውንት
ይኖራቸዋል - አንደኛው
ዊንዶውስ ኤክስ.ፒ
የሚገቡበት (Windows XP local account)
ሲሆን፣ ሁለተኛው ደሞ
ዶሜይን ሎግኢን
አካውንት (ወይም Domain account)
ናቸው፣ የሎካል
አካውንት የሚኖረው
በነዚህ Windows XP
ኮምፒዩተሮች ውስጥ
ሶፍትዌር
ለመገንባት፣
ኮንፊዩግሬሽን
ለማካሄድና ሲስተም
ነክ ለውጦችን
ለመፍጠር በዚሁ ሎካል
አካውንት በተለይም
አድምንስትሬተር
ሀይል (privileges) ያለው።
ነገር ግን በኔትወርክ
ውስጥ ሎግ አድርጎ
ድራይቫቸውን
ለማየት፣ ፋይላቸውን
በኔትወርክ የግል
ቦታቸው (drive) ለማስፈር
በሳንባ ውስጥ
የፈጠርነውን
ፓስወርዳቸውን ወይም
ዶሜይን አካውንት
መጠቀም አለባቸው
ማለት ነው።
አካውንት
ስንፈጥር፣ የሊኒክስ
አካውንትና የሳንባ
አካውንት መፍጠር
አስፈላጊ ነው።
በመጀመሪያ
የሊኒክስ አካውንትን
ለመፍጠር
የሚከተለውን
እናከናውናለን።
[root@aabole01 home]# useradd -m username
ከላይ username የሚለው ተራ በተራ
የአራቱም ሰራተኞች
ዩዘር አካውንት
ይሆናል። ቀጥሎም
ለአራቱም ፓስወርድ
እንፈጥራለን።
[root@aabole01 home]# passwd username
Changing password for username.
New password: XXXXXXXX
Re-enter new password፡ XXXXXXXX
ከላይ
ፓስዎርድ ሁለቴ ታይፕ
አድርገን Enter የሚለውን
ከኪቦርዱ ስንጫን፣
የሚከተለውን መልክት
እናያለን፡
password changed
ቀጥሎም
የሳንባ ፓስወርድ
ለያንዳንዳቸው ዩዘር
አካውንቶች
እናበጃለን ከታች
እንደሚታየው።
[Root@aabole01 home]# smbpasswd -a username
New SMB password:
Retype new SMB password:
ቀጥሎም ግሩፕ አካውንት
ለማርኬቲንግ፣
ለአካውንቲንግ፣ፋይናንስና
አፕልኬሽን
ፕሮግራሞች
የሚሰፍሩበት
እንፈጥራለን።
ይህንን
ለማድረግ መጀመሪያ
የነዚህን
ዳይሬክተሪዎች
እንፈጥራለን፡
[root@aabole01 home]# mkdir -p /usr/{accounts,markets,finances,apps}
ቀጥለንም
የያንዳንዳቸውን
ተጠቃሚዎች
የሚሰሩበትን የግል
ስፍራ (ወይም privileges)
በሀርድ ድራይቩ ውስጥ
እናዘጋጃለን
በሚከተለው መልክ፡
ማርኬቲንግ = ደላላው
አካውንቲንግ = ብልሀት
ፋይናንስ = አቶ አደፍርስ፣
በተጨማሪም የሁሉም
መብት (privileges) አላቸው።
ሴክሬተሪ = ስራብዙ፣ የአቶ
አደፍርስ ረዳት
ስለሆነች የሁሉንም
ማንበብ (read) መብት
አላት፣ ምክንያቱም
ለአቶ አደፍርስን
ስለምትረዳ፣ ነገር
ግን ባሉት ፋይሎች ላይ
መጻፍ ሳይሆን ማንበብ
ብቻ ነው የምትችለው።
ቀጥለንም
ሁሉም የሚጋሩትን
ዲይሬክተሪ
እንሰራለን
[root@aabole01 home]# mkdir -p /home/share
ይህ የሚጋሩት ዳይሬክተሪ
በሙሉ ፋይሎቹን
የማንበብ (read)
በውስጣቸው መጻፍ
እንዲቻል (write) እና
ክንውን ማካሄድ
እንዲችሉ (execute) መብትን
እንዲያገኙ
አደርጋለሁ። ነገር
ግን ከላይ
የተጠቀሱትን
ዳይሬክተሪዎች
በሚመለከት።
|
|
|
|
|
|
|
[root@aabole01 home]# chmod 777 /home/share
ቀጥሎም
የየግሩፕ ፋይሎችን
እንደመብቻቸው
እናስቀምጣለን፡
[root@aabole01 home]# chown delalaw:accounts /usr/accounts
[root@aabole01 home]# chown belahat:markets /usr/ markets
[root@aabole01 home]# chown adeferes:finance /usr/finance
አፕልኬሽኖችን
በሚመለከት፣ ወደፊት
ከጊዜ ወደጊዜ
አስፈልጊ የሆኑ
ፕሮግራሞች (ለምሳሌም
አካውንቲንግ፣
ማይክሮሶፍት ኦፊስ፣
ማይክሮሶፍት ፋክስ፣
ወዘተ)በሙሉ
የሚሰፍሩት
በሚከተለው
ዳይሬክተሪ ውስጥ
ስለሚሆን በዶሜይን
አካውንታቸው ማየት
እንጂ ፕሮግራሞቹን
ኢንስቶል ማድረግ
አይችሉም፣
ምክንያቱም የዶሜይን
አካውንት መብት
አልሰጠኋቸውም፣
ከአቶ አደፍርስ
በቀር። ስለዚህ
የሚቀጥለው
የሚያሳየን በሙሉ
ማየት ይችላሉ ነገር
ግን ፕሮግራሞቹን
ኤክስኪውት ማድረግ
አይችሉም። ስለዚህም
በዶሜይን
አካውንታቸው
ሪከርሲቭሊ ማየት
እንጂ ሌላ ነገር
ማድረግ አይችሉም
የሚቀጥለው መስመር
እንደሚያሳየው።
[root@aabole01 home]# chmod -R /usr/apps
ከዚህ ሌላ አቶ አደፍርስ
ሁሉንም ማየት
ስላለባቸው ከላይ በsmb.conf
ፋይል ውስጥ ለ
ሰራቸኞቹ ባስገባነው
ፕራይቬት የሀርድ
ድራይቭ ቦታ ሼር
አክሰስ እንዲኖራቸው
በ valid users መሰረት
አስገብተናቸዋል
በዋናው ኮንፊግሬሽን
ፋይል ውስጥ።
ቀጥለንም
የቴክስት ፋይል
በመፍጠር ለሁሉም
ኮምፒዩተሮች የጊዜ
(ወይም time) ሰርቪስና፣
ድራይቭ፣
የምንጋራውን፣ የግል
ፋይሎችና
ዳይሬክተሪዎች
እንዲሰጣቸው
አደርጋለሁ። የፋይሉ
ስም፡ logon.bat ሲሆን
ይህንን ፋይል በ /home/netlogon
እናስቀምጠዋለን።
ይህም ፋይል
የሚከተሉትን
ይይዛል።
net time \\ aabolesmb01 /set /yes
net use h: /home
net use p: \\ aabolesmb01\apps
ቀጥለንም
የዊንዶውስ ሲስተም
ዶሜይን አካውንቶችን
በሊኒክስ አካውንቶች
የሚገነባልን አንድ
ፋይል እንሰራና በ /etc/samba
ዳይሬክተሪ ውስጥ
በሚስማማን ፋይል ስም
(እኔ linux-win-map.sh የሚል ስያሜ
ሰጠሁት። ይህም ፋይል
በውስጡ የሚይዘው
እንደሚከተለው
ይሆናል።
#!/bin/bash
#
linux-win-map.sh
#
Create UNIX groups
groupadd markets
groupadd accounts
groupadd finance
groupadd apps
groupadd share
#
Map Windows Domain Groups to UNIX groups
net groupmap modify ntgroup="Domain Admins" unixgroup=root
net groupmap modify ntgroup="Domain Users" unixgroup=users
net groupmap modify ntgroup="Domain Guests" unixgroup=nobody
#
Add Functional Domain Groups
net groupmap add ntgroup=" Markets Dept " unixgroup`= markets type=d
net groupmap add ntgroup=" Accounts Dept" unixgroup= accounts type=d
net groupmap add ntgroup=" Financial Services" unixgroup= finance type=d
net groupmap add ntgroup=" Applications " unixgroup= apps type=d
ከላይ
የሚታየውን linux-win-map.sh
ፋይል በ /etc/samba
ዳይሬክተሪ ውስጥ
አሰፈርኩት። እዚህ
ላይ ከፋይሉ ስም በኋላ
.sh ሼል ፕሮግራም
መሆኑን ነው
የሚያበስረን፣
አስፈላጊና መረሳት
የሌለበት ነው።
ካስቀመጥን በኋላ
ግንባታ (ወይም execution)
በማድረግ ዊንዶውስን
በሊኒክስ ካርታ (map)
እናደርጋለን።
ይህንንም ፋይል
ግንባታ ስናደርግ
የሚከተለውን
በሊኒክስ ተርምናል
ውስጥ ታይፕ
አደረግሁ።
[root@aabole01 home]# ./linux-win-map.sh
ይህ ፕሮግራም በርካታ
ነገሮችን በስክሪኑ
ላይ ሲሰራ እናያለን
እንዳበቃም
የሚከተለውን በዚሁ
የሊኒክስ ተርምና ላይ
ታይፕ እናደርጋለን፡
[root@aabole01 home]# net groupmap list | sort
ይህ በትክክል ማፕ
የተደረጉትን
ሰርቪሶች በሙሉ
ያሳየናል።
ቀጥለንም
የፕሪንቲንግ
ሲስተማችንን እና
የሎጊን ዲይሬክተሪ
እናስተካክላለን።
የሳንባ የፕሪንቲንግ
ስፑል (spool) እንፈጥራለን
ከሌለ። የሳንባን
ዳይሬክተሪ በ /var/spool
ዳይሬክተሪ ውስጥ
ከመፍጠራችን በፊት
መኖሩን ማረጋግጥ
ይገባል። ብዙውን ጊዜ
ይኖራል። ነገር ግን
ከሌለ የሚከተለውን
ማድረግ ነው ከሊኒክስ
ተርምናል፡
[root@aabole01 home]# mkdir -p /var/spool/samba
[root@aabole01 home]# mkdir -p /home/{netlogon,profiles}
[root@aabole01 home]# chown -R root:root /var/spool/samba
[root@aabole01 home]# chmod a+rwxt /var/spool/samba
[root@aabole01 home]# chown -R root : root /home/netlogon
[root@aabole01 home]# chown -R root : root /home/profiles
አሁን ሁሉን ነገር ጨረስን፣
ይሚቀጥለው ሳንባንና
ፕሪንቲንግ
አገልግሎቶች
ማስነሳት ይሆናል።
[root@aabole01 home]# chkconfig smb on
[root@aabole01 home]# chkconfig cups on
[root@aabole01 home]# /etc/rc.d/init.d/smb restart
[root@aabole01 home]# /etc/rc.d/init.d/cups restart
ዲ.ኤች.ሲ.ፒ
ሰርቪስ ግንባታ
ከላይ
የሳንባ ሰርቨርን
ብንባታ ጨረስን፣
እንዳየነውም እዚህ
ሳንባ ሰርቨር ውስጥ
ከገነባናቸው
ሰርቪሶች ውስጥ አንዱ
የዲ.ኤች.ሲ.ፒ ሰርቪስ
ሲሆን፣ ይህም
አገልግሎቱ አይፒ
አድራሻዎችን
ኮንትራት (ወይም ሊስ)
መስጠት ይሆናል።
ዲ.ኤች.ሲ.ፒ ሰርቨር
እንዴት ይሰራል?
ይህ ሰርቨር በውስጡ
በተዘጋጀው ፖሊሲ
መሰረት ለተገናኙት
ኮምፒዩተሮች ሁሉ
አይፒ አድራሻ
ይሰጣል። አይፒ
አድራሻ ከዚህ ሰርቨር
ጋር ለተገናኙት
ኮምፒዩተሮች ሁሉ
በሁለት መልክ
ይመደብላቸዋል።
- ዳይናሚክ አይፒ
አድራሻ - ይህ
የሚመደበው
ካልተያዙት
አድራሻዎች ውስጥ
የዲ.ኤች.ሲ.ፒ
ሰርቨሩን ዴስክቶፕ
ኮምፒዩተሮች
ሲጠይቁት
አውቶማቲካሊ
ይመድብላቸዋል።
- ስታቲክ አይፒ
አድራሻ - ይህ የአይፒ
ምደባ ደሞ፣
ኮምፒዩተሮቹ
ቅድም-አይፒ አድራሻ
ተሰጥቶዋቸዋል።
ሆኖም የተገናኙት
ኔትወርክ በሚሰጠው
አይፒ አድራሻ ገደብ
ውስጥ መሆን አለበት
ብሎም በዲኤች.ሲ.ፒ
ሰርቨሩ ውስት ስታቲክ
የተመደበለት
ኮምፒዩተር
ተጠቅሷል።
ኮምፒዩተሩ
ጠፍቶ ሲነሳ
የኔትወርክ ግንኙነት
ካለው የ ዲ.ኤች.ሲ.ፒ
ፍለጋ (DHCPDISCOVR ወይም BOOTREQUEST)
ያካሂዳል። ሰርቨሩም
ይህ ሲግናል ሲደርሰው
አይፒ አድራሻ ሊመድብ
ይሞክራል።
በተገናኘው ኔትወርክ
ሰግመንት ውስጥ
ያልተያዘ አይፒ
አድራሻ ሊመድብ
ይፈልግለታል። ነገር
ግን ኮምፒዩተሩ ከዚህ
በፊት ተገናኝቶ
ከነበረና አይፒ
አድራሻ ኮንትራት
ጊዜው በተሰጠው የጊዜ
ገደብ ውስጥ ከሆነ፣
ኮምፒዩተሩ ይህንን
አይፒ አድራሻ
ይጠይቃል
እንዲመደብለት።
ካልተይዘም
የዲ.ኤች.ሲ.ፒ ሰርቨሩ
ይወዲያው
ይፈቅድለታል።
የአይፒ አድራሻ ችግር
ከሌለ በቀር ብሎም
የፖሊሲ ሴታፕ
ስናደርግ ኮምፒዩተር
ከጠፋ አይፒ
አድራሻዎችን
እንዲሰበስብ የተለየ
መመሪያ ለዲ.ኤች.ሲ.ፒ
ሰርቨሩ ካልሰጠነው
በቀር፣ ማነኛውም
ኮምፒዩተር ኮንትራት
ጊዜው ካላለቀ በቀር
ሰርቨሩ ይህንን አይፒ
አድራሻ
ይጠብቅለታል። ነገር
ግን የኮንትራት ጊዜው
ሲደርስ፣ ሰርቨሩ
በመጀመሪያ ይህንን
ኮምፒዩተር መኖሩን
ያረጋግጣል፣
ከምፒዩተሩ ካለ
ኮንትራት እንዲቀጥል
ይጠይቃል። በመስመሩ
ላይ ከሌለ (ምናልባት
ኮምፒዩተሩ ከጠፋ፣
ኔትወርክ ኬብሉ
ከተነቀለ፣ የመሰሉት
ሁኔታዎች) ሰርቨሩ
ይህንን አይፒ አድራሻ
በመሰብሰብ አይፒ
አድራሻ ለሚጠይቁ
ያስቀምጠዋል።
በመጠኑም ተግባሩ
ግልጽ ይሆናል ብዬ
አምናለሁ። የበለጠ
ለመረዳት በጥልቀት
የተጻፉ መጽሐፍቶች
ስለሚኖሩ እንሱን
መመርመር ነው።
ዲ.ኤች.ሲ.ፒ ሴታፕ
የዲ.ኤች.ሲ.ፒ
ክንውን
ብኮንፊግሬሽን ፋይል (dhcpd.conf)
ውስት በርካታ
መስመሮች
የተነጋገርንባቸውን
ክስተቶች
የሚያከናውን
እናስገባን ፋይሉን
ሴቭ እንደርገዋለን።
ከዚሁም ጋረ ኮንትራት
(ሊስ) የሚያደርግበት
ሎግ ቫይ ሰርቨሩን
በምንገነባበት ጊዜ
ይቀመጣል፣ ከሌለም
አስፈላጊው
ዳይሬክተሪ ውስጥ ሄዶ
ማረጋገጥ
ያስፈልጋል።
የሚከተለው
የዲ.ኤች.ሲ.ፒ
ኮንፊግሬሽን ፋይል (dhcpd.conf)
ይዘት ነው።
#
/etc/dhcpd.conf
options domain-name-servers 192.168.0.2
default-lease-time 6000;
max-lease-time 72000;
#
የአንድ ሳብኔት ዋጋ
subnet 192.168.0.0 subnet mask 255.255.255.0
{
range 192.168.0.1 192.168.0.200
option routers 192.168.0.1;
options broadcast-address 192.168.0.255;
default-lease-time 6000;
max-lease-time 7200;
}
host smb {
hardware ethernet 0x:xx:xx:xx:xx:xx;
fixed-address 192.168.0.3;
}
host printer {
hardware ethernet 0x:x1:x2:x3:x4:x5;
fixed-address 192.168.0.4;
}
ቀጥለን
የምናደርገው
የዲ.ኤች.ሲ.ፒ
ኮንትራት መዝጋቢ
ፋይል (lease file) መኖሩን
እናረጋግጣለን፣
አለዚያም
እንፈጥራለን - /var/db/dhcpd.leases.
ይህንንም ለማድረግ
ከኮማንድላየን ላይ
ሆነን የሚከተለውን
ታይፕ እናደርጋለን፡
[root@aabole01 home]# touch /var/db/dhcpd.leases
ከዚህ በኋላ ዲ.ኤች.ሲ.ፒ
ሰርቨርን ሁሌም
ስራውን አውቶማቲካሊ
እንዲጀምር
እናደርገዋለን፡
[root@aabole01 home]# service dhcpd start
[root@aabole01 home]# chkconfig add dhcpd on
ዴስክቶፕ
ኮምፒዩተር ሴታፕ
ምጀመሪያ
አቶ አደፍርስ ቢሮ ሄጄ
ኮምፒዩተሩን
አስነሳሁት። አዲስም
ስለሆነ የላይሰንስና
ሬጂስትሬሽን
ጥያቄዎች መጡ፣
እነሱንም
አልፋቸዋለሁ።
ኢንተርኔቱ ሲዘጋጅ
የሚስተካከል ስለሆነ
ነው። ቀጥሎም በሎካል
አድምንስትሬተር
ፓስወርድ ኮምፒዩተሩ
ውስጥ ከገባሁ በኋላ
ማይክሮሶፍት ኦፊስን
(ወርድ፣ ኤክስኤል፣
ፓወርፖይንት፣
አክሰስና አውትሉክ)
ኢንስቶል አደርግሁ።
በሁሉም ኮምፒዩተሮች
ተመሳሳይ አድርጌ
ጨረስሁ።
ቀጥለንም
በሁሉም ኮምፒዩተሮች
ዶሜይን ሴታ
አደረግሁ፣ ይህንን
በሚከተለው ሁኔታ
ተጠናቀቀ።
Start->right click on My Computer ->Properties -> Click on Computer Name -> Change -> Click
on Domain radio button -> type aabolesmb01-> Click OK
ከዚያም ዩዘር
ስምና ፓስወርድ
ይጠይቀናል፡
የምንከተው የዶሜይን
አድምንስትሬተሩን
ይሆናል።
ከዚያም OK የሚለውን ስንጫን
መቀበሉን የሚገልጽ
ትንሽ ሳጥን
ትመጣልች፣ እሱላይም
OK የሚለውን ክሊክ
እናደርግና
እንዘጋዋለ።
ኮምፒዩተሩ
ውስጥ የሴኪዩሪቲና
ሌላም ሲስተም ነክ
ለውጦች ስለተደረጉ
ኮምፒዩተሩን ዘግተን
እንድናስነሳ
ይጠይቀናል፣ እሱም
ላይ OK የሚለውን ክሊክ
ስናደርግ ኮምፒዩተሩ
ወዲያው ሁሉን ነገር
ይዘጋል፣ ከዚያም ሙሉ
በሙሉ ያጠፋና
እንደገና ይጀምራል።
አሁን ሎጊን ለማድረግ
<CTRL><ALT><DEL>
ን ከኪቦርዱ ላይ
እንጫናለን የሚጠይቅ
ቦክስ ይመጣል እሱም
ላይ በሰጠው መመሪያ
መሰረት ከተጫንን
በኋላ ዩዘር ስም
የሚለው ላይ የአቶ
አደፍርስን ዩዘር
ሰም፣ ፓስወርድ
የሚለው ላይ ለአቶ
አደፍርስ ሳንባ
ፓስወርድ ውስጥ
የፈጠርኩትን
ፓስወርድና በሶስተኛ
ደረጃ የዶሜይን ምርጫ
ሲሆን እሱ ላይ ክሊክ
በማድረግ aabolesmb01
እንመርጣለን፣ ይህም
የሳምባ ዶሜይናችን
ነው። ነገር ግን
በተለምዶ ለመጀመሪያ
ጊዜ የሚታየው
የኮምፒዩተሩ ስም
ነው። ከዚያም OK
የሚለውን ክሊክ
ስናደርግ ወዲያው
ዴስክቶፑ
የሚጀምርበትን ሂደት
እናያለን። በዚህ
ሂደት ውስጥ ጥቁር
ቦክስ ወይም ዶስ
ኮማንድ ላየን (MSDOS)
የሚመስል ይመጣል፣
የሚያሳየንም የባች
ፕሮግራም ሂደት
ሲሆን፣ ከላይ
ለዶሜይን ሎግኢን
በሊኒክስ ውስጥ
ያዘጋጀነው ስክሪፕት
ሂደት ነው። ይህም አቶ
አደፍርስን
የሚለይበት ሴታፕ
ክንውን ይሆናል።
ቀጥለንም
በ My Computer ሁለቴ ክሊክ
አድርገን ስንከፍት
በውስጡ ከሌሎቹ
ድራይቮች ጋር H:
ድርይቭን እናያለን።
ይህ ድራይቭ ስያሜው
ለሁሉም ያው ይሁን
እንጂ እያንዳንዳቸው
ኮምፒዩተሮች የግል
ዲስክ ቦታቸው ነው።
ስለዚህ በዚህ ድራይቭ
ውስጥ የሚቀመጥ
ፋይልና ዳይሬክተሪ
ሁሉ ለአቶ አደፍርስ
ብቻ ነው የሚታየው።
ለምሳሌ አካውንቲንግ
የሚሰራው መጥቶ አቶ
አደፍርስ ኮምፒዩተር
ውስጥ ሎግ ቢያደርግ፣
የሚኖረው በሙሉ የሱ
አካውንት ነው፣
የሚታየውም H: ድራይቭ
ከስያሜ ተመሳሳይነት
በቀር ከሌሎቹ
አካውንቶች H: ድራይቭ
ጋር ምንም ንክኪ
የለውም። መሰረታዊ
አገልግሎቱ
ተንቀሳቃሽ ፕሮፋይል
(Roaming Profiles) በሳንባ ውስጥ
ሴታፕ ስላደረግን
ሲሆን፣ በዚህ
ኔትወርክ ውስጥ ሎግ
በምናደርግበት
ኮምፒዩተር ሁሉ
አካውንታችንና
የሰራናቸው ስራዎች
ሁሉ ይከተሉናል።
ሎካል ኔትወርካችንን
አስመልክቶ ሁሉም
ነገር ተጠናቀቀ።
የሚቀረው
ኢንተርኔት ግንኙነት
ይሆናል እሱንም ከቴሌ
ጋር በመፈረም
የማያቋርጥ ዳያላፕ
አካውንት (dedicated dialup connection)
ለመትከል ተነጋግሬ
ጨርሼያለሁ። እሱ ደሞ
የነግ ስራዬ ይሆናል።
ትልቅ
ስራ ነው
ያገባደድኩት፤
ይህንን ሁሉ ሳደርግ 10
ሰአት አልፎዋል።
ምሳም አልበላሁ፣
ጠዋት ቁርስ ብቻ
ያደረግሁ ነኝ። እስቲ
ቦሌ አካባቢ ካሉት ውብ
ምግብ ቤቶች አንዱ ጋ
ልሂድና ምሳየን
እየበላሁ
የጨረስኳቸውን ሁሉ
በመገምገም፣
ያልተሰሩትን ደሞ
አንዳንድ ኖቶች
አወጣለሁ ብሎ ከልቡ
ጋር ከተነጋገረ
በኋላ፣ ሁሉንም
ኮምፒዩተሮች
አጠፋፍቶ በሩን
ቆላልፎ ወጣ። የዛሬው
ስራ በዚህ ተጠናቀቀ፣
የነገ ሰው ይበለን
እያለ ጉዞውን
ወዳሰበው ሬስቶራንት
አመራ።
ከልቡ
ውስጥ የነበረ ምግብ
ቤትም ደረሰና
በመስተንግዶ
ተቀመጠ፣ ከቅጽበት
አስተናጋጇ መጣችና
ምን ልታዘዝ ብላ
ጠየቀችው፣ ትንሽ ሞቅ
ያለ ቀን ነበረና አፉን
በማጣጣም፣ እስቲ
ቀዝቃዛ የታሸገ ውሀ
በመጀመሪያ
እፈልጋለሁ ብሎ
በመቀጠል፣
የሚመገበውንም
አዘዘ። አስተናጋጇም
ትእዛዙን ወስዳ
ሄደች። አቶ ለጋሱ
ወደመኪናው በመሄድ
ኖትፓድ ከላፕቶፑ
ቦርሳ አውጥቶ ይዞ
ተመለሰ። ከልቡ ጋርም
እንደተነጋገረው
የሚከተሉትን እቅዶች
ማውጣትና ማወዳደር
ጀመረ።
ኢንተርኔቱን
ግንኙነት በሚመለከት
በሁለት መልክ መስራት
ይቻላል ብሎ ያስባል።
ለማወዳደርም
እንዲያመቸው
በጽሁፍና በስእል
እንደሚሆን ማስቀመጥ
ይጀመራል። ያሰበውን
ያሰራር ዘይቤ በሁለት
መልክ ያስቀምጠዋል።
|
|
|
- በየቢሮው ያሉትን
ኮምፒዩተሮች
በሚያገናኘው ዳያላፕ
ሞደም አማካኝነት
ከኢንተርኔት ጋር
ግንኙነት ማድረግ
ነው። ይህም ሂደት
ደረጃ በደረጃ
ሲቀመጥ፡
- አይፒ አድራሻ
የሚሰጠው ኢንተርኔት
ሰርቪሱ ሲሆን፣
ዳያላፕ ሞደሙ ይህንን
አድራሻ ቀጥታ
ለኮምፒዩተሮቹ
ያሳልፋል። ስለዚህም
እያንዳንዳቸው
ኮምፒዩተሮች
የፐብሊክ አይፒ
አድራሻ ይኖራቸዋል
ማለት ነው። ይህንን
አይነት ግንኙነት
ኢንተርኔት የሚሰጥው
(ቴሌ ማለት ነው)
ከጥቅም አንጻር ሆነ
ትራፊን ከመጨመር
አንጻር ለማስተናገድ
በእቅዳቸው ውስጥ
አይደለምና
አብዛኛውን ጊዜ ችግር
ሊኖር ይችላል።
- ሞደሙ የሚመጣን
ትራፊክ ማጣራት (filter)
ከክንውኖቹ ውስጥ
አይደልምና
እያንዳንዳቸው
ኮምፒዩተሮች
እራሳቸውን መጠበቅ
አለባቸው ከተለያዩ
አጥፊ (malicious)
ሶፍትዌሮች። በዚህ
አጋጣሚ ሳንባ
የሚያስተናግደው
ለኔትወርኩ ደህንነት
(security) ሳይሆን፣ በዚህ
ኔትወርክ ውስጥ
የተፈቀደላቸው ሰዎች
ብቻ በውስጡ ያለውን
ቁሳቁሶች (resources)
እንዲጠቀሙ ማድረግ
ነው።
- ራውተር መጠቀም -
ይህ ከውጪ አንጻር
በጣም ከባድ ይሆናል።
ስለዚህ ይህ አማራጭ
ወደጎን
እናስቀምጠዋለን።
ምናልባት ትልቅ
መዋቅር ሲኖረን
የምንመለስበት
ይሆናል።
- የሊኒክስ ራውተር
መትከል - ይህንን
ከሳንባ ጋር አንድ ላይ
ማድረግ እንችላለን።
ነገር ግን ጥንቃቄ
ጉድለትን ሊያስከት
ይችላል፣ ብሎም የጓሮ
በር ሊከፍትብን
የሚችልበትን ሁኔታ
መፍጠር ይሆናል።
ምክንያቱም ማነኛውም
ትራፊክ በዚህ ሳንባ
ሰርቨር ላይ
ስለሚመላለስ
የሚጋለጥበት ሁኔት
እንዳይከሰት ጥንቃቄ
ማድረግ ነው።
ስለዚህም በዚህ ላይ
የማስበው፣ ሌላ ትንሽ
ኮምፒዩተር፣
የተጣመር በመግዛት
የሊኒክስን ራውተር
መገንባት ይሆናል። ይህ የተለየ
የሚያደርገው
ምንድነው?
- ዋናው ከዚህ
የምንፈልገው ከላይ
በቁጥር 1.a ላይ
የተቀመጠውን
የፐብሊክ አይፒ
አድራሻ ይህ
ኮምፒዩተር ብቻ ነው
የሚያገኘው፣ የቀሩት
ኮምፒዩተሮች
ማነኛውንም ትራፊክ
የሚቀያየሩት በዚህ
ሊኒክስ ራውተር
አማካኝነት ስለሆነ
እሱ ደሞ የኔትወርክ
ትርጉም የሚሰጥበት
ሰንጠረዥ (ወይም NAT - Network Address
Translation) ስላለው፣ ከሎካል
ኔትወርካችን
የሚመጣን ጥያቄ በዚሁ
አይፒ ሰንጠረዥ ካጣራ
በኋላ በያንዳንዳቸው
ኮምፒዩተሮች ስም ሆኖ
ከኢንተርኔት ሰርቪስ
ሰጪው በተሰጠችው
አንድ አይፒ አድራሻ
መሰረት በማድረግ
መልክቶችን
ይቀያየራል።
- ይህንን ሁሉ
ለማድረግ በዚህ
ሊኒክስ ራውተር
ኮምፒዩተር ውስጥ
አንድ ኔትወርክ ካርድ
(ወይም Ethernet Card) ና አንድ
ዳያልአፕ ሞደም
ይኖራሉ።
- እንዴት
ለኮምፒዩተሮቹ
የኢንተርኔት
ግንኙነቱ ይደርሳል?
በመጀመሪያ ዳያልአፕ
ሞደሙ ከኢንተርኔት
ሰርቨሩ ጋር ግንኙነት
ያደርግና የፐብሊክ
አይፒ አድራሻ
ያገኛል። ከዚያም
ሞደሙ የፈጠረውን
ግንኙነት በኔትወርክ
ካርዱ አማካኝነት
ከ/ወደ ስዊቹ
በማቀባበል
ኮሞፒዩተሮቹ
ከኢንተርኔት
የሚፈልጉትን
እንዲቀያየሩ
ይሆናል። ስለዚህም
ይህ ራውቲንግ
ኮምፒዩተር የሚሰራው
እንፎርሜሽኖችን
ከኢንተርኔታ ጋር
የሎካል ኔትወርካችን
እንዲቀያየር ማድረግ
ይሆናል። አጠቃላይ
ኔትወርካችን ሲያልቅ
የሚኖረውን ግንኙነት
በሚቀጥለው ስእል
ይጠቃለላል።

ስለዚህ
የሁለተኛው ሊኒክስ
ሰርቨር (ራውተሩ ማለት
ነው) ወደፊት ሀይ
ስፒድ ግንኙነት
ሲኖረን በቀላሉ
ሞደሙን በሌላ
ኔትወርክ ካርድ
በመቀየር፣ መጠነኛ
ስክሪፕት ሞድፊኬሽን
በማድረግ ምንም
አይነት ለውጥ
ሳናደርግ የፍጥነት
እድገትን ማድረግ
ይቻላል።
ይህንን
ሲያሰላ አስተናጋጇ
ምሳውን አመጣችለት፣
በደንብ አጣፍጦ
ምግቡን ጨረስና
ወሃውንም ከጠጣ በኋላ
የነገ ሰው ይበለን
እያለ ክፍያውን ከፍሎ
ወጣ።
ሁለተኛውን
ሰርቨር - ራውተር
ግንባታ
በነጋታው
ጠዋት ተነስቼ
ወደቢሮው አመራሁ፣
እግረመንገዴንም
መልካም ማኪያቶ
ከጠጣሁ በኋላ
የመጨረሻውን ግንባታ
ክንውን ለመጨረስ
ወደቢሮ አመራሁ።
እንደደረስኩም
በቀትታ ወደሰርቨር
ክፍል በማምራት
ለራውተር የገዝሁትን
አዲስ ኮምፒዩተር
የሃይል ምንጩን
በምጫን አስነሳሁት።
ይህም ኮምፒዩተር
ዊንዶውስ ኤክስ.ፒ
ስለሆነ እሱን
አስወግደን
ወደሊኒክስ
እንቀይረዋለን።
ባጠቃላይ የዛሬው
ሰርቨር ግንባታ
ከኢንተርኔት
የሚመጣን ወይም
ወደኢንተርኔት
የሚሄድን ትራፊክ
ማቀያየር የሚያስችል
ከመሆኑም በላይ፣
የኔትወርኩን
ደህንነት (ወይም security)፣
ከውጭ በሚመጣውንና
የሚወጣውን
መቆጣጠርም ይሆናል።
እያንዳንዳቸውን
ደረጃ በደረጃ
እመጣባቸዋለሁ።
ይህንን ሰርቨር
ስንገነባ ከላይ
በመጀመሪያው ሰርቨር
ላይ የሰራነውን
መሰረት በማድረግ
በፍጥነት የሰርቨሩን
መሰረት በሁለተኛው
ኮምፒዩተር ላይ
አስቀምጬ ጨረስኩ።
ከላይ የተከልናቸውን
ሰርቢሶች፣ ለምሳሌም
ሳንባን፣ በዚህኛው
ውስጥ አናስቀምጥም።
የምናደርገው ባዶ
ሰርቨር ብቻ ነው
የገነባሁት። ሪሞት
አክሰስ እንዲኖረን
ግን VNC ሰርቨርን
አስቀምጠናል
በሁለተኛው ሰርቨር።
ሁሉን ከጨረስን
በኋላ፣ የራውተሩን
ሶፍትዌር
እንገነባለን፣ ይህም
ሶፍትዌር ስሙ - ዚብራ
(zebra) ይባላል።
በነገራችን ላይ
የዚህን ሰርቨር
ኮምፒዩተር ስም - aabolertr01
ብየዋለሁ።
መጠነኛ ዚብራ ራውተር ትውውቅ
ዚብራ
TCP/IP ላይ የተመሰረት
የራውቲንግ ሶፍትዌር
ሲሆን በስሩ BGP-4, BGP-4+, OSPFv2, OSPFv3,
RIPv1, RIPv2, እና RIPng ሲደግፍ፣
የራውት ክንውን
እንዲካሄድ
ያስችላል።
ኢንተርኔት
የተመሰረተው
በቲሲፒ/አይፒ
ፕሮቶኮል ላይ ስለሆነ
መላውን አለም
ይሸፍናል ማለት
ይቻላል። ስለዚህም
ከኢንተርኔት ጋር
ግንኙነት ስንፈጥርና
መልክቶችን
ስንቀያየር፣ እነዚህ
መልክቶች
የቲሲፒ/አይፒ
ራውቲንግ ክንውን
ያዘሉ ብዙ ራውተሮችን
ያልፋሉ።
በመጀመሪያ
ይህንን ሶፍትዌር
የጻፉት Kunihiro Ishiguro እና Yoshinari
Yoshikawa በ 1996 ሲሆን፣ ባሁኑ
ሰአት በነዚሁ
መስራቾች አማካኝነት
-አይፒ ኢንፊዩዥን
በሚባል ካንፓኒ ስር
ሆኖ በርካታ ፈቃደኛ
ኢንጂኒየርስ
በነጻ/ክፍት ሶፍትዌር
ፋውንዴሽን ስር ሆኖ
እድገቱ በፍጥነት
በመካሄድ ላይ
ይገኛል።
የተግባሩ
መሰረት በፕሮቶኮሎች
ላይ የተመሰረተ
ሲሆን፣ በሚያመች
መልክ የራውቲንግ
ጸባያቸውን መቀየር
እንድንችል
ይፈቅድልናል።
ይህ የዚብራ ሶፍትዌር
እስካሁን ከቀረቡት
ራውቲንግ ሶፍትዌሮች
ሁሉ ከሲስኮ ራውተር
ጋር በይዞታ በጣም
ይቀራረባል። ምንም
እንኳን አንዳንድ
ሁኔታዎች ለየት ቢሉም
ለኔትወርክ
ባለሙያዎች የሲስኮን
ተመሳሳይ ጸባይ
መስጠቱ እንግዳ
እንዳይሆኑ
ያደርጋቸዋል።
ይህንን
ሰርቨር በተከልኩበት
ጊዜ የነበረው ዚብራ
ራውተር ቨርዥን 0.95a
ሲሆን ከትንሽ እስከ
መካከለኛ
ካንፓኒዎችን
ለመደገፍ አይነተኛ
ምርጫ ነው (ማለትም
በርካታ ሺህ የሚሆኑ
ሰራተኞች ያሉትን
መ/ቤት ያጠቃልላል)።
ይህንን
ሰርቪስ ግንባታ
ስናካሂድ ቀደም ካሉት
ለየት ባለ መልክ
ይሆናል። ምክንያቱም
እስካሁን የገነባነው
ባይነሪ ሶፍትዌር
ሲሆን ይህም
ቅድመ-ቅምጥ (pre-configured)
ነው። ነገር ግን ዚብራ
ራውተርን ስንገነባ
አስፈላጊ ቱሎች
እንዲኖሩ ለማድረግ
በጥሬ-ደንብ (ወይም source code)
ግንባታን ላይ
እንመሰረታለን።
ይህንንም ለማድረግ
የሚከተሉትን
አከናወንኩ።
- ከዚብራ ህጋዊ
ዌብሳይት (http://www.zebra.org)
ሶፍትዌሩን ዳውንሎድ
አድርጌ በሲዲ
ያሰፈርኩት ጥሬ-ደንብ
ሶፍትዌር ስላለኝ
እሱን ሲዲ-ሮም ውስጥ
ከተትኩ። የዚህ
ጥሬ-ደንብ መጠን
ምናልባት ከ 4-6MB
ይሆናል።
- ቀጥሎም ሲዲ-ሮሙ
ምንም እንኳን
የሊኒክስ ሲስተማችን
ቢያውቀውም ዲቫይሱን
እንጂ የከተትነውን
ሲዲ አያውቀም፣
ስለዚህ እሱን መጫን (mount
ማድረግ) አለብን።
ይህንንም ለማድረግ
ከኮማንድ ላየን ሆኜ
የሚከተለውን
ተጠቀምኩ።
[root@ aabolertr01 root]# mount /dev/cdrom /mnt/cdrom
- ከዚያም ሲዲው ላይ
ያለውን ፋይል
ወደሎካል ሲስተማችን
ኮፒ አደረግነው
[root@ aabolertr01 root]# cp mnt/cdrom/zebra-<version>.tar.gz /usr/local/src
- ይህን ፕሮግራም ባንድ ፋይል
ታስሮ የተቀመጠ ሲሆን
እሱን መበተን
አለብን፣ በመጀመሪያ
ፋይሉ ወዳለበት
ዳይሬክተሪ ማመልከት
አለበን ፕሮግራሙን
ለመበተን
[root@ aabolertr01 root]# cd /usr/local/src
- ከዚያም ፕሮግራሙን
እንበትነዋለን፣
ይህም የሚበተኑት
ፋይሎች ባንድ
ዳይሬክተሪ ይሆናሉ
[root@ aabolertr01 root]# tar -xvfz zebra-<version>.tar.gz
- አሁን የዚብራን
ዳይሬክተሪ
እናያለን፣ ወደሱም
በመሄድ ሶፍትዌር
ግንባታ
እናደርጋለን።
[root@ aabolertr01 root]# cd zebra-<version>
[root@ aabolertr01 root]# ./configure
[root@ aabolertr01 root]# make
[root@ aabolertr01 root]# make install
አሁን ግንባታችንን
ጨረስን፣ ፋይሎቹንና
ፕሮግራሞቹን
በየቦታው አስፍሮ
ለመጨረስ ትንሽ ጊዜ
ይፈጃል። ዚብራ
በተለያዩ
ዳይሬክተሪዎች ውስጥ
አስፈላጊ ፋይሎችን
ያስቀምጥልናል፣
ቀጥዬም የማደርገው
ኮንፊዩግሬሽን
ይሆናል።
- ወደኮንፊግሬሽን ከመሄዳችን በፊት ማጣራት ያለብን ነገር /etc/services በሚለው ፋይል ውስጥ የሚከተሉት መኖራቸውን እናረጋግጣለን።
zebrasrv 2600/tcp # zebra service
zebra 2601/tcp # zebra vty
ripd 2602/tcp # RIPd vty
ripngd 2603/tcp # RIPngd vty
ospfd 2604/tcp # OSPFd vty
bgpd 2605/tcp # BGPd vty
ospf6d 2606/tcp # OSPF6d vty
ከዚያም ዚብራ እንዲካሄድ እናደርጋለን፣ ከታች እንደሚታየው፡
[root@ aabolertr01 root]# zebra –d
[root@ aabolertr01 root]# rip -d
- በሁለት መልክ
ኮንፊግሬሽን ማካሄድ
ይቻላል፣ አንደኛው
ልክ እንደሲስኮ
ራውተር ሴታፕ
የቴልኔት ግንኙነት (telnet
session) ከሊኒክስ ተርምናል
ሳጥን ውስጥ ሆነን
ሲሆን፣ ሌላው መንገድ
ደሞ በቀጥታ ፋይሎችን
በመፍጠር የዚብራን
ፕሮቶኮሎች (ማለትም
የምንፈልገውን)
ሰርቪስ በመጀመር
ይሆናል። እኔ
የሁለተኛውን
ለመጠቀም
መርጬያለሁ፣ ፈጣንና
ቀላል ስለሆነ።
- ቀጥለንም /etc/zebra
ዳይሬክተሪ በመሄድ
ለስራችን
የምንፈልጋቸው ሶስት
ፋይሎች ሲሆኑ፣
እነሱን እንሰራለን።
ምናልባትም zebra.conf እና vtysh.conf
የሚሊት ሊኖሩ
ይችላሉ። የሁለተኛው
ፋይል ምንም ለውጥ
አናደርግም ነገር ግን
የምንሰራቸውን
የራውቲንግ ክንውን በ
zebra.conf እና ripd.conf ፋይሎች
ውስጥ ሲሆን
አስፈላጊውን ኮዶች
በውስጣቸው
እናስቀምጣለን።
ነገር ግን ለስራችን
መሰረት በትክክል
ዲዛይንድ የሆነ
ንድፈሃሳብ
ያስፈልጋልና፣
ለዚህም በምን መልክ
ስራው ከንድፈ-ሃሳብ
ግንዛቤ ወደተግባር
እንደሚሸጋገር
እንመለከታለን።
- በመጀመሪያ ይህ
ራውተር ከኢንተርኔት
ይገናኛል በዳያልአፕ
ግንኙነት።
- ቀጥሎም ከዳያልአፕ
ግንኙነታችን
የሚመጣውን/የሚሄደውን
ትራፊክ በቀጥታ
ከኔትወርክ አዳፕተሩ
ጋረ እንዲቀያየር
በዚብራ አማካኝነት
እናደርጋለን።
- ዳያላፕ ሞደሙ
የኢንተርኔት ትራፊክ
የሰጠውን ይቀበላል፣
ይህም አይፒ አድራሻን
ጨምሮ ማለት ነው።
ከተለመደው ዳያልአፕ
ግንኙነት ውጭ
የሚጠይቀው የተለየ
ትራፍክ ማስተካከል (traffic
shaping) አይኖርም። ነገር
ግን የመጣውን ትራፊክ
ለፕራይቬት
ኔትወርካችን ለማዋል
ስለሆነ ጥረታችን
ይህንን የኢንተርኔት
ትራፊክ መጠቀም
እንድንችል ነው
የምናደርገው ሴታፕ።
ባጠቃላይም
ኢንተርኔት ሰርቨሩ
ዚብራ ራውተራችንን
ልክ እንደማንኛውም
የኢንተርኔት ተጠቃሚ
እንጂ በጀርባው ማስክ
ያደረገውን
የፕራይቬት
ኔትወርካችንን
አያውቀውም።
- ቀጥሎም ራውተሩ
ውስጥ ላለው ኔትወርክ
አዳፕተር ቋሚ ፕራቬት
ስታቲክ አይፒ አድራሻ
መመደብ ሲሆን፣
በየክፍሉ ያሉት
ኮምፒዩተሮች
ከሚያገኙት አይፒ
አድራሽ ገድብ ውስጥ
ነው (ማለትም ይህ
አድራሻ 192.168.0. ኔትወርክ
ውስጥ ሲሆን
ልዩነታቸው
ፕሪንተሩ፣ የሳንባ
ሰርቨርና ይህ ራውተር
ቋሚ አድራሻ ከዚሁ
ኔትወርክ አድራሻ
ውስጥ ሰጥቼያቸዋለሁ።
- በሌላ በኩል ደሞ
በየክፍሉ ያሉት
ኮምፒዩተሮች
ዳይናሚክ አይፒ ነው
የሚረከቡት
ከዲ.ኤች.ሲ.ፒ
ሰርቨሩ። ከላይ
እንዳየነው የሳንባ
ሰርቨራችን
ዲ.ኤች.ሲ.ፒ ተግባርን
ስለሚጨምር፣ ይህ
ሳንባ ከፋይል
ፕሪንቲንግ፣
ዶሜይንና ግሩፕ
ጥየቃዎችን ከማሟላት
ሌላ በየክፍሉ ላሉት
ኮምፒዩተሮች አይፒ
አድራሻ ያከራያል።
እነዚህ በየክፍሉ
ያሉት ኮምፒዩተሮች
አጥፍተን እንደገና
ስናስነሳቸው (ወይም reboot
ሲሆኑ) የሚኖራቸው
አይፒ አድራሻ ሌላ
ሊሆን ይችላል። በኛ
አጋጣሚ የአይፒ
አድራሻ ብዛት (ወይም pool)
ችግር ስለሌለብን፣
ወይም ያሉን
ኮምፒዩተሮች አምስት
ብቻ ስለሆኑና፣
የአይፒ አድራሻ መጠኑ
254 ስለሆነ የአይፒ
አድራሻ ውጥረት
ለአሁን
አይኖርብንምና
የተጠቀምንምበት
አይፒ አድራሻ መልሶ
ሊሰጠን ይችላል፣
ምክንያቱም
ኮምፒዩተራችን
እንደገና ሲነሳ
አጥብተነው፣
የመጀመሪያ ጥየቃው፣
ተመሳሳ&
|
| | |